Tuesday, December 29, 2015

የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዮናታን_ተስፋዬ‬ ተሰወረ

የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊና የማህበራዊ ገፅ ንቁ ተሳታፊ የሆነው ዮናታን_ተስፋዬ‬ትላንት ጠዋት ለስራ ወደ ሚያስተምርበት ትምህርት ቤት ከጠዋቱ አንድ ሰዓት እንደወጣ ወላጅ እናቱ የተናገሩ ሲሆን አክለውም ከትምህርት ቤቱ ለማጣራት እንደሞከሩና ጠዋት ወደ ስራ ገብቶ እንደነበር እንደነገሩዋቸውና መቼ እንደወጣ እንዳላወቁ እንደነገሩዋቸው አሳውቀዋል የዮናታን የእጅ ስልክ ሲደወልለት የሚጠራ ሲሆን ነገር ግን አይነሳም የፌስ ቡክ አካውንቱም ከ18፡00 ሰዓታት በፊት ከኦንላይን እንደወጣ ያሳያል እስካሁንም ወደ ቤቱ አልተመለሰም የት እንዳለ ቤተሰቦቹም ሆኑ ጋደኞቹ አፈላልገውት ማግኘት አልቻሉም። በአንድ አሳቻ ቦታ ለሻይ እረፍት ሲወጣ ወይም ከሚያስተምርበት ቦታ የህወሀት ቅልብ ወንበዴዎች አፍነውት ነው ተብሎ ይገመታል።

No comments:

Post a Comment