Monday, December 14, 2015

በወገኔ ላይ አልተኩስም ያሉ ወታደሮች ዩኒፎርማቸውን እያቃጠሉ ሕዝቡን እየተቀላቀሉት ነው ተባለ

በኦሮሚያ እና በ150 የኦሮሚያ ከተሞች የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ቁጣን ለማብረድ መንግስት ወታደሮቹን አሰማርቶ ትናንት ብቻ በም ዕራብ ሸዋ እና በደቡብ ም ዕራብ ሸዋ 25 ሰዎችን መግደሉን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም:: ዛሬ ከሃገር ቤት የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ወደ ሕዝቤ አልተኩስም ያሉ ሕወሓት የሚያዘው መከላከያ ሚ/ር ወታደሮች በየቦታው ዩኒፎርማቸውን በአደባባይ በማቃጠል ሕዝቡን እየተቀላቀሉ ነው::

በኦሮሚያ የተነሳው ከፍተኛ የሕዝብ ቁጣ ዛሬም ቀጥሎ በም ዕራብ ሸዋ ባኮ እንዲሁም በም ዕራብ ወለጋ በነጆ ወረዳ በወራ ጅሩ; አቹማ ጎሪ እና ጊዳ ከተሞች ተቃውሞ ሲሰማ ውሏል;; ቡራዩ ከተማ የመለስተኛ ሁልተኛ ደረጃ ተማሪዎች ወታደሮች እንዳይገቡ በድንጋይ መንግዱን አጥረውታል::

No comments:

Post a Comment