Monday, December 28, 2015

የካራቶሪው ባለቤት መሬቴን ትነኩና የህንድን ሃያልነት ታያላችሁ ሲሉ የመንግስት ባለስልጣናትን አስጠነቀቁ

ታኀሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጋምቤላ 300 ሺ ሄክታር መሬት ተሰጥቷቸው ለማልማት ባለመቻላቸው ከፍተኛ ትችት የሚቀርብባቸው የካሩቱሪ አግሮ ፕሮዳክትስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ መሥራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሳይ ራማክሪሽና ከሪፖርትር ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ የጋምቤላ ክልል መንግስት በግድ ሳይፈልጉ በፈለጉት ዋጋ ከፍለው 300 ሺ ሄክታር መሬት እንደሰጧቸው ተናግረዋል። እኔ የጠየቁት 10 ሺ ሄክታር ብቻ ነው ያሉት ባለሃብቱ፣ እነሱ ግን 300 ሺ ሄክታር ካልወሰድ ብለው ሰጡኝ ብለዋል።
መሬታቸውን ማንም እንደማይነጥቃቸው የተናገሩት ባለሀብቱ “መሬቴን ንኩና የህንድን ሃያልነት ታያላችሁ። ይሄ ማስጠንቀቂያ ነው። የእስካሁኑ የሚበቃ መሰለኝ። ራሴን መከላከል አያስፈልግኝም። ባለስልጣናት መሬቴን ከነኩ በዓለምአቀፉ ፍርድ ቤት ውጤቱን ያገኙታል ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
“የጋምቤላ ክልል መንግሥት ካቢኔ በሙሉ ስብሰባ ከተቀመጠ በኋላ 10 ሺሕ ብቻማ አንሰጥህም አሉኝ፡፡ እኔ ግን አቅሜ ይኸው ብቻ እንደሆነ ገልጬላቸዋለሁ፡፡ከስብሰባቸው በኋላ 300 ሺሕ ሔክታር መሬት እንደሚሰጡኝ ይልቁንም እኔ በማምንበት ዋጋ እንድከፍል፣ ከዚያ ያነሰ መሬት ግን እንደማይሰጡኝ አስታወቁ፡፡ ምርጫ አልነበረኝም፡፡” ተቀበልኩ የሚሉት ባለሃብቱ፣ በመካከለኛ ደረጃ ያሉ ባለስልጣናት ፖለቲካውን ተገን አድርገው ሊያሰሩኝ አልቻሉም ብለዋል።
ሼክ ሙሃመድ አላሙዲንንም በኢትዮጵያ ውስጥ ራሳቸውን የቻሉ መንግስት ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment