Monday, December 14, 2015

በአ/አ የነዳጅ እጥረት ተከሰተ ፡፡

ታኀሳስ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ ማደያዎች ነዳጅ በሚፈልጉ አሽከርካሪዎች ተጨናንቀው ውለዋል።

እንዲህ አይነቱ ክስተት አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ቢሆንም፣የዛሬው ከሌሎቹ ጊዜያት የሚለየው በበርካታ ማደያዎች ነዳጅ ባለመኖሩ ነው፡፡ የችግሩ ምክንያት በግልጽ ባይታወቅም አንዳንድ ምንጮች በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ከተከሰተው
የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ነዳጅ መግባት ባለመቻሉ ነው ብለዋል።

No comments:

Post a Comment