Monday, December 14, 2015

በሱዳን እና በኢትዮጵያ ጠረፍ ከፍተኛ ውጥረት ሰፍኗል።

45 ሱዳናውያን ባልታወቁ ታጣቂዎች ተጠልፈው ወደ ኢትዮጵያ ተወሰዱብኝ ስትል ጸረ ሰላም ያለቻቸውን በሰሜን ጎንደር የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ዓውግዛለች፥ በተጨማሪም ከ90 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ጠርፍ ተሻግረው ሸፈቱ ሲል እሄው የሱዳን አረብኛ ጋዜጣ ዘግቧል።

ጋዜጣው እንደዘገበው 45 ሱዳናውያን ዜጎቿ በታጣቂዎች ተይዘው፥ በኢትዮጵያ መሬት ውስጥ በመተማ ዓካባቢ እንደሚገኙና የሱዳን መንግሥት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በመተባበር እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ ዓሳውቋል ሲል ይገልጻል፥
የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን አሳልፎ ከሚሰጠው የድንበር ማካለል ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሱዳን ተወልደው ያደጉና በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ድንበር ተሻግረው በርሃ መግባታቸው ታውቋል።
በሰሜን ጎንደር የሱዳን ጠረፍ ዙሪያ ከፍተኛ የዓመጽ እንቅስቃሴ እንዳለና የሕዝቡ ቁጣ ግለቱ እየበረታ መሆኑ ከዓካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፥

No comments:

Post a Comment