Monday, December 28, 2015

የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበርን ለማካለል የተጀመረ ስራ እንደሌለ የኮምኒኬሽንና ሚዲያ ባለሙያዎች ደጋግመው እንዲሰሩ የአቶ ጌታቸው ረዳ ጽ/ቤት አሳሰበ፡፡

ታኀሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመንግስት ኮምንኬሽን ጽ/ቤት ለኮምኒኬሽን ባለሙያዎችና ለጋዜጠኞች ባሰራጨው የመንግስት የሳምንቱ አቋም መግለጫ በኢትዮ ሱዳን ድንበር ጉዳይ የተጀመረ ስራ እንደሌለ እንዲናገሩ አቅጣጫ አስቀምጧል።
“መንግስት ሁሉም የኢትዮጵያ ድንበሮችን የማካለል ስራ ጠቃሚ መሆኑን ይረዳል”ያለው ፣ የአቋም መግለጫው፣ ሆኖም የኢትዮ-ሱዳንን ድንበር ለማካለል አሁን ምንም የተደረገ ስምምነት የለም።» በማለት በሱዳን ሚዲያዎች በተደጋጋሚ እየተዘገበ ያለውን ጉዳይ ለማስተባበል ሞክሯል፡፡
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፈው ሳምንት ለኢህአዴግ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር የኢትዮ ሱዳን ድንበር አካላይ የጋራ ኮምሽን ተቋቁሞ እየሰራ መሆኑን አምነዋል። አያይዘውም በድንበሩ አካባቢ የሚኖሩ «ሽፍቶች» ያሉዋቸው ኢትዮጵያዊን ወደ ሱዳን ገብተው ግድያ እንደሚፈጽሙ ተናግረዋል፡፡
አቶ ሃይለማርያም የኢትዮጵያ ባለሀብቶችና አንዳንድ አርሶአደሮች ሱዳን ክልል ውስጥ ገብተው መሬት እያረሱ መሆኑን መናገራቸው፣ ጠ/ሚኒስትርነታቸው ለኢትዮጵያ ነው ወይስ ለሱዳን የሚል ጥያቄ አስነስቶባቸው ሰንብቷል።

No comments:

Post a Comment