Monday, December 14, 2015

ከአዲስ አበባ ወደ አምቦ መስመር የሚወስደው መንገድ ቡራዩ ላይ በሕዝብ እንደተዘጋ ነው::

በዛሬው እለት የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን የሚቃወመው የቡራዩ ከተማ ጠዋት የጀመረው የሕዝብ ተቃውሞ ተባብሶ ቀጥሏል::የወያኔ አገዛዝ ወታደሮች ሕዝቡ ላይ እየተኮሱ ነው:: የመንግስት መስሪያ ቤቶች ትምህርት ቤቶች እና መደብሮች የተዘጉ ሲሆን እስካሁን የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት 3 ሰዎች በወያኔ ተገድለዋል::እንዲሁም – በጂማዓርጆ ወለጋ – በጫንጮ – በዴሳ – ሜታሮቢ- ጊንጪ – ነጆ- ሚናሌ- እላ ጎሮ – ሜታ- ነቀምት – ደምቢዶሎ ቀለሜ- ጊንዶ -አስጎሪ -ደንዲ -ቱሉ ቦጃ -ጫሊያ- አቺማ ጆሪ -ጊዳ -ዋራ ጂሩ – ሆሮ ጉዱሩ ተቃውሞው ተፋፍሞ ቀጥሏል::በጀልዱ ጎጆ ከተማ ሰባት ሰዎች ከአግኣዚ ጦር በተተኮሰ ጥይት ቆስለዋል::

No comments:

Post a Comment