Saturday, December 19, 2015

የጎንደር አማራ በሶስት ግንባር ከጠላቶቹ ጋርበጀግንነት እየተፋለመ ነው:

gonder
1 _ በምእራብ በኩል መሬት ቆርሶ ሊወስድ ከተዘጋጀ ከሱዳን ጦር ሰራዊት ጋር የሞት ሽረት ትግል እያደረገ ነው ።
2 _ በሰሜን ግንባር አባይ ወልዱ እያስታጠቀ ከሚያስገባው የትግሬ ታጣቂ ጋር እየተፋለመ ነው ።
3 _ ሶስተኛው ግንባር መሬት ቆርሶ ለመስጠት ከወሰነው የወያኔ ሰራዊት ጋር “መሬቴን የምትሰጠው ሬሳየን ተራምደህ እንጅ እስትንፋሴ እያለ የነፋሲለደስንና የመይሳውን መሬት ንክች አታደርጋትም ” እያለ እየተፋለመ ነው ።
*** ይህ በእንድህ እያለ የሱዳን መንግስት ” ከ 50 በላይ ዜጎቼ መሬቱ የኛ ነው በሚሉ ኢትዮጵያውያን ታጣቂወች ታፍነው ተወስደውብኛል ። ዜጎቼን ለማስለቀቅ የሱዳን መከላከያ ሰራዊት ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር እየሰራ ነው የሚል አስገራሚ መግለጫ እውጥቷል ።
በሌላ በኩል የወልቃይት ማህበረሰብም “በትግራውያን የማንነት ዘረፋ ስለተፈፀመብን ወደ ትክክለኛው ማንነታችን አማራነታችን ለመመለስ በምናደርገው ፍልሚያ የአማራ ህዝብ ሊረዳን ይገባል ” እያለ ነው ።
እኛም ከዚህ ለነፃነቱ ለማንነቱ እና ለሀገሩ እየታገለ ካለው ህዝብ ጎን ልንሰለፍና አጋርነታችንን ልናሳየው ይገባል ።

No comments:

Post a Comment