Tuesday, December 19, 2017

በኦሮምያ ክልል የሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ዛሬም ቀጥለው ውለዋል

በጨለንቆ በመከላከያ ሰራዊት አባላት የተገደሉ የኦሮሞ ተወላጆችን ለመዘከር እንዲሁም መከላከያ ከክልሉ እንዲወጣ ለመጠየቅ የሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ዛሬም በመቱና በደምቢደሎ ተደርገዋል።
ተማሪዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች በአንድነት በመውጣት በመከላከያ እና በሶማሊ ልዩ ሃይል እየደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ አውግዘዋል። መከላከያም ከክልሉ እንዲወጣ ጥያቄ አድርገዋል። 
በክልሉ የሚካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች መቀጠላቸው በስልጣን ላይ ባለው የህወሃት ኢህአዴግ አገዛዝ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል። በክልሉ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ሰራዊት መሰማራት ህዝቡን ይበልጥ እያስቆጣው መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች ያሳያሉ።

No comments:

Post a Comment