Wednesday, December 6, 2017

ለኢሳት ቤተሰቦች/የቅርብ ደጋፊዎች የቀረበ ጥሪ!!!

ሁላችንም እንደምናውቀው፣ ኢሳት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነፃነትና ዲሞክራሲ የሚያደርገውን ትግል በማገዝ ረገድ ካለው ሚና አንፃር ያለው የፋይናንስ ምንጭ እና መጠን ውሱንነት አለው።
ይህንን በአግባቡ ስንመረምር፣ ኢሳት አስተማማኝ እና ተከታታይነት ያለው የፋይናንስ ምንጭ ኖሮት ወርሃዊ ወጪውን መሸፈን እንዲችል በአሁኑ ሰዓት በእጃችን ላይ የሚገኘው አስተማማኝ የፋይናንስ ምንጭ አማራጭ - ተቀባባይ/የማይቋረጥ (automated) ቋሚ የወርሃዊ ድጋፍ/ክፍያ ሆኖ እናገኘዋለን። ይህንን የኢሳትን ወርሃዊ ወጪ በአሁኑ ሰዓት የኢሳት ቤተሰቦች/የቅርብ ደጋፊዎች የሆኑ በሙሉ በሚያደርጉት ተቀባባይ/የማይቋረጥ (automated) ቋሚ ወርሃዊ ድጋፍ/ክፍያ ማሟላት ይቻላል የሚል ዕምነት አለን።

በመሆኑም፣ የኢሳትን አስተዋጽዖና ሚና የዋጋ ደረጃ የምትረዱ እና የቋሚ ወርሃዊ ድጋፍ/ክፍያ ያልፈጸማችሁ የኢሳት ቤተሰቦች/የቅርብ የኢሳት ደጋፊዎች፣ አሁኑኑ ይህንን ቋሚ ወርሃዊ ድጋፍ/ክፍያ እንድትጀምሩ አደራ ጭምር እንጠይቃለን። ለዚህም ዛሬውኑ ይመዝገቡ፣ ያስመዝግቡ!!!
ኢሳትን በአስተማማኝ የፋይናንስ መሠረት ላይ በማቆም ጠንካራ የሚዲያ ተቋም መሆን እንዲችል ሁላችንም የድርሻችንን እናደርግ!!!
ይህንንም መልዕክት ለሁሉም የኢሳት ቤተሰቦች/የቅርብ ደጋፊዎች በማስተላለፍ ምላሽ እንዲሰጡ ባለማቋረጥ እንገፋፋ/እናበረታታ!!!
ኢሳት የ21ኛዋ ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ አንጋፋ እና አውራ የሕዝብ፣ በሕዝብ፣ ለሕዝብ የቆመ የሚዲያ ተቋም ሆኖ ይቀጥላል!!!��የኢሳት ደጋፊ የሆንን ሁሉ ዛሬ በድረ-ገጻችን ላይ ወይም በስልክ ቀጥር ‎‎1-888-772-3728 ext 4 በመደወል የ”ኢሳት ቋሚ ወርሃዊ ክፍያ አባል” በመሆን ይመዝገቡ! ወዳጆችዎንም ያስመዝግቡ!�https://app.mobilecause.com/form/Fcv8ZQ

No comments:

Post a Comment