Wednesday, December 20, 2017

የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ማይክ ኮፍማን የራሱን ህዝብ የሚያሸብር መንግስት የአሜሪካ አጋር መሆን አይገባውም ሲሉ ተናገሩ

Image may contain: 1 person, suitየአሜሪካ ኮንግረስ አባል ማይክ ኮፍማን የራሱን ህዝብ የሚያሸብር መንግስት የአሜሪካ አጋር መሆን አይገባውም ሲሉ ተናገሩ። ኮፍማን ይህንን ያሉት በአሜሪካ የኮሎራዶ ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ዴንቨር ባለፈው ቅዳሜ ኤች አር 128 በመባል የሚታወቀውን ረቂቅ ህግ አስመልክቶ በተዘጋጀው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ነበር። ኢትዮጵያና አሜሪካ በጋራ የሚያደርጉት የጸረ ሽብር እንቅስቃሴ አደጋ ላይ ይወድቃል በሚል ማስፈራሪያ ህጉ እንዲጨናገፍ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
በስብሰባው ላይ የተገኙት የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ሃብታሙ አያሌውና የኢሳት ዋና ዳይሬክተር አበበ ገላውም ኢትዮጵያውያን በውጭም ይሁን በሀገር ቤት በሚደረገው ትግል በንቃት እንዲሳተፉና ድጋፍ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል። በዴንቨር የኤች አር 128 አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ኮፍማን ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት ለሚያደርጉት አስተዋጻኦ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ለሳቸውና ለረዳታቸው ሚስዝ አሮራ ኦግም ሽልማት አበርክተዋል። ኮንግረስ ማን ኮፍማን በበኩላቸው በዴንቨር ነዋሪ የሆኑትና በዚህ እንቅስቃሴ ቁልፍ ሚና ለሚጫወቱት ለዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ ሽልማት አበርክተዋል። ይሁንና ዲያቆን ዮሴፍ ሽልማቱም እውቅናውም አይገባኝም በማለት ከእኔ ይልቅ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት ሲታገል ተይዞ ኢሰብአዊ ግፍና ሰቆቃ ለተፈጸመበት ሃብታሙ አያሌው ሽልማቱን በገጸ በረከት አበርክተዋል።

No comments:

Post a Comment