Wednesday, December 6, 2017

የሕወሃት የስለላ ተቋማት አንድ በእስራኤል የሚገኝ ድርጅት የሚያቀርበውን የስለላ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክን፣አንድ የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪንና የአንድ ጠበቃን ኮምፒዩተሮች ሲሰልል እንደነበር ሲትዝን ላብ የተባለው ተቋም አጋለጠ።

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 27/2010) የሕወሃት የስለላ ተቋማት አንድ በእስራኤል የሚገኝ ድርጅት የሚያቀርበውን የስለላ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክን፣አንድ የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪንና የአንድ ጠበቃን ኮምፒዩተሮች ሲሰልል እንደነበር ሲትዝን ላብ የተባለው ተቋም አጋለጠ። በአሜሪካ በሚገኙ የኢትዮጵያውያን ነጻ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ላይ፣በግለሰቦችና ሌሎች ድርጅቶች ላይም የስለላ ተግባር መፈጸሙ ተጋልጧል። በሲትዝን ላብ የሚገኝ አንድ ግለሰብም የጥቃቱ ሰለባ መሆኑ ታውቋል። ሲትዝን ላብ እንደ ሕወሃት ያሉ አምባገነን መንግስታት በግለሰቦችና በተቋማት ላይ የሚያደርጉትን ስለላ እየተከታተለ የሚያጋልጥ ተቋም ነው። የሕወሃት መንግስት የኢንተርኔት የስለላ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በአሜሪካ በሚገኙ የኢትዮጵያውያን ነጻ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ላይ፣በግለሰቦችና ሌሎች ድርጅቶች ላይ የስለላ ተግባር መፈጸሙ ተጋልጧል። ሲትዝን ላብ የተሰኘውና እንደ ሕወሃት ያሉ አምባገነን መንግስታት በግለሰቦችና በተቋማት ላይ የሚያደርጉትን ስለላ እየተከታተለ የሚያጋልጥ ተቋም ዛሬ አገኘሁት ያለውን መረጃ ይፋ አድርጓል። እንደ ተቋሙ መረጃ የሕወሃት የስለላ ተቋማት አንድ በእስራኤል የሚገኝ ድርጅት የሚያቀርበውን የስለላ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክን፣አንድ የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪን እንዲሁም አንድ ጠበቃን ኮምፒዩተሮች ሲሰልል እንደነበር ታውቋል። በሲትዝን ላብ የሚገኝ አንድ ግለሰብም የጥቃቱ ሰለባ መሆኑን አስታውቋል። ሲትዝን ላብ በምርመራ እንደደረሰበት ከሆነ የሕወሃት መንግስት የስለላ ተቋማት በ20 ሀገራት የሚገኙ የግለሰብና የተቋማት ኮምፒዩተሮችን ሰብረው በመግባት ሲሰልሉ እንደነበርና ከነዚህም ውስጥ የኤርትራ መንግስት ተቋማትና ድርጅቶች ይገኙባቸዋል። በእስራኤል የሚገኘውንና ሳይበር ቢት በመባል የሚታወቀው የኢንተርኔት ደህንነት ተቋም የሚያቀርበውንና ፒ ኤስ ኤስ በመባል የሚታወቀው የስለላ ዘዴ ጥቃት ወደሚፈጸምባቸው የግለሰብና የድርጅት ኮምፒዩተሮች ለመሰለል የሚውሉ አደገኛ ፋይሎችን የያዙ ኢሜሎችና ሌሎች መልዕክቶች ሲላኩ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ፒ ኤስ ኤስ በስለላና በሕግ ማስከበር ለተሰማሩ ድርጅቶች የሚቀርብ መሆኑ ታውቋል። ሲትዝን ላብ በሪፖርቱ ሲዘረዝር ለግለሰቦች በሚላኩ በነዚሁ ኢሜይሎች ተቀባዮቹ የቪዲዮ መልዕክቱን ሲጫኑ አዶቤ ፍላሽ አፕዴት እንዲያደርጉ ይመራል። ነገር ግን ይህ አዶቤ ፍላሽ የሚለው መስፈንጥር የተደበቀ የስለላ ፕሮግራም ወደ ያዘ ዌብ ሳይት እንደሚወስድ ተደርሶበታል። በሌሎች ኮምፒዩተሮች ላይ ደግሞ ተጠቃሚዎች በቀጥታ የአዶቤ ፒ ዲ ኤፍ ራይተር ኢንስቶል እንዲያደርጉ ይጠይቃል። ይህ ፒ ዲ ኤፍ ራይተር ግን የእስራኤሉ ሳይበር ቢት የሚያመርተው ቴክኖሎጂ መሆኑ ተረጋግጧል። በሲትዝን ላብ ምርመራ መሰረት የስለላ ፕሮግራሙ መነሻም ኢትዮጵያ መሆኗ ተረጋግጧል። ስለላው በካናዳ፣አሜሪካ፣አውስትራሊያ፣ሕንድ፣እንግሊዝ፣ጣሊያን፣ጀርመን፣ኖርዌይ፣ጃፓንእንዲሁም በአፍሪካ ኬንያ፣ዩጋንዳ፣ኤርትራ፣ሩዋንዳ፣ግብጽ በሚኖሩ ግለሰቦች ላይ ሲያነጣጥር እንደነበር ታውቋል። ከመካከለኛው ምስራቅ ደግሞ የመንና ኳታር ይገኙበታል። የህወሃት የስለላ ተቋም ሳይበር ቢት የተባለውን የእስራኤል የስለላ ቴክኖሎጂ ድርጅት ሲጠቀም ይህ የመጀሪያው አይደለም። በአውሮፓውያኑ 2015 የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የተባለው የሕወሃት የስለላ ቢሮ በኢሳት ጋዜጠኞች ኮምፒዩተሮች ላይ ተመሳሳይ ስለላ መፈጸሙ ይታወሳል። ፊን ፊሸር የተባለን የስለላ ፕሮግራም በአንድ አሜሪካ በሚኖር የስርአቱ ተቃዋሚ ግለሰብ ላይ በመፈጸሙ የሕወሃት መንግስት በአሜሪካ ፍርድ ቤት ተከሶ እንደነበርም ይታወቃል። ሲትዝን ላብ በሪፖርቱ እንዳሰፈረው ባለፈው አንድ አመት የሕወሃት መንግስት የኢንተርኔት ስለላ ጥቃት በዋናነት የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክና በውስጡ በሚሰሩ ግለሰቦች እንዲሁም የኦሮሞ አክቲቪስቶች ላይ ማነጣጠሩ ታውቋል። ከጥቂት ወራት በፊት የሲትዝን ላብ ባለሙያዎች የኢሳት ኮምፒዩተሮችን ፈትሸው የጥቃቱ ሰለባ አለመሆናቸውን አረጋግጠዋል።

No comments:

Post a Comment