Sunday, December 3, 2017

በወልድያ በተነሳው ተቃውሞ የተለያዩ የንግድ ቤቶች እና መኪኖች ጉዳት ድርሶባቸዋል

በወልድያ በተነሳው ተቃውሞ የተለያዩ የንግድ ቤቶች እና መኪኖች ጉዳት ድርሶባቸዋል። የአጋዚ ወታደሮችና የክልሉ ፖሊሶች በአስለቃሽ ጭስ ህዝቡን ለመበተን ሞክረዋል። ተቃውሞው በመቀሌና በወልድያ እግር ኳስ ደጋፊዎች መካከል ይነሳ እንጅ፣ አጠቃላይ በኢትዮጵያ ከሚታየው ተቃውሞ ጋር የሚያያዝ መሆኑን ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ይሰሙ ከነበሩት መፈክሮች መካከል " ወያኔ ይውደም፣ በወያኔ አንገዛም"የሚሉት ይገኙበታል። በአሁኑ ሰአት ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ እየተሰማ ነው።

No comments:

Post a Comment