Tuesday, December 5, 2017

የሱዳን ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቀው መግባታቸውን ተከትሎ አገዛዙ ልኡካኑን ወደ ካርቱም ላከ

 ትናንት በከባድ መሳሪያዎች የታጀበ የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ በመግባት የተለያዩ ቀበሌዎችን ከያዘ በሁዋላ፣ የአገዛዙ ባለስልጣናት የልኡካን ቡድን ወደ ካርቱም መላካቸውን ምንጮች ገልጸዋል። 
በሁለቱ አገራት ወታደራዊ መሪዎች መካከል ዛሬም ንግግር የተጀመረ ሲሆን፣ የሱዳን ወታደሮች ከላይ ትእዛዝ ከመጣላቸው እንደሚወጡ ቢያስታውቁም፣ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ሰአት ድረስ ከኢትዮጵያ ግዛት ለቀው አልወጡም።
የመከላከያ ሰራዊቱ የአገሪቱን ዳር ድንበር ለማስከበር እስካሁን የወሰደው እርምጃ የለም፡፡ ጦሩን ሱዳኖች ወደ ተቆጣጠሩት አካባቢ ማስጠጋቱን ግን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። 
ወረራው ለመከላከል በርካታ የኢትዮጵያ ሰራዊት ወደ ቦታው መንቀሳቀሱ የኣከባቢው ነዋሪዎች ገልፀውልናል።

ሱዳን የኢትዮጵያ ሉኣላውነት ጥሳ በመግባት መሬት በወረራ ተቆጣጥራለች።
ሱዳኖቹ አካባቢውን የያዙት በገዳሪፍ ገዢ በመታዘዛቸው መሆኑን ቢናገሩም፣ በገዳሪፍ አስተዳደር በኩል እስካሁን የተሰጠ መግለጫ የለም።
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ እየተካሄደበት ባለበት በዚህ ወቅት፣ ሱዳን ጦሩዋን ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ለምን እንደፈለገች ግልጽ የሆነ ነገር የለም።
ሁለቱ አገራት ከዚህ ቀደም በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ሃይሎችን ለመቆጣጠር በሚል በጋራ ለመስራት ስምምነት ማድረጋቸው ይታወቃል። የሱዳን ጦር አካባቢውን እንደወረረ ምሽግ መስራት መጀመሩ እና ከኢትዮጵያ ድንበር እንዲወጣ ሲጠየቅ “ከላይ በተሰጠ ትዕዛዝ ነው የገባሁት” ማለቱ የአሁኑ ወረራ ከዚህ ስምምነት ውጭ መሆኑን እንደሚያሳይ ምንጮች ይገልጻሉ።

No comments:

Post a Comment