Wednesday, December 20, 2017

በአማሮ ወረዳ ያለው ግጭት እንደቀጠለ ነው

በአማሮ ወረዳ ያለው ግጭት እንደቀጠለ ነው
ከድንበር ማካለል ጋር በተያያዘ በአገዛዙ ካድሬዎች የተነሳውና ላለፉት 5 ወራት መፍትሄ አጥቶ የቀጠለው የኮሬና የጉጂ ኦሮሞ ብሔረሰቦች ግጭት፣ ትናንት ታህሳስ 10 ቀን 2010 ዓም ምሽት ላይ በተነሳዉ ግጭት በአማሮ ወረዳ ጎልቤ በተባለዉ ቀበሌ ሁለት የኮሬ አርሶ አደሮች ሕይወት ሲጠፋ በተመሳሳይ ሰዓትም በቡርጂ እና በጉጂ መሃል ግጭቱ ተቀስቅሶ አንድ የቡርጂ አርሶ አደር ወዲያዉ ሕይወቱ ሲያልፍ አንዱ ደግሞ ቆስሏል።
ባለፈው እሁድና ሰኞ የደኢህዴን ልሳን በሆነዉ የደቡብ ቲቪ ግጭቱ እንደቆመና የህዝብ ለህዝብ እርቅ እንደተደረገ በተነገረ ማግስት አዲስ ግጭት መቀስቀሱ ህዝቡን ይበልጥ እያነጋገረው ነው።
በአካባቢዉ የአጋዚ እና የአካባቢ ፖሊስ አባላት ቢኖሩም ግጭቱን ለማስቆም ፈቃደኝነት አላሳዩም። ከሐምሌ 16 2009 ዓም ወዲህ በኮሬ በኩል ብቻ የሞቱት ዜጎች ቁጥር 30 መድረሱና የቆሰሉት ደግሞ 64 መሆናቸዉ ታውቋል፡፡
በመንገድና በመብራት እጦት ሲሰቃይ በነበረዉ ሕብረሰብ ላይ የኔትዎርክና ኢንተርኔት አገልግሎት በመቋረጡም ከማህበራዊ ሚዲያዎች የሃገሪቷን ሁኔታ ሲከታተሉ ለነበሩት የህብረተሰብ ክፍሎች ተጨማሪ እንግልት እንደፈጠረባቸው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

No comments:

Post a Comment