Tuesday, December 26, 2017

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የፓርላማ አባላትን በጥብቅ የደህንነት ጥበቃ ስር ሆነው አነጋገሩ።

በኢህአዴግ አባላት የተያዘው ፓርላማ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መደበኛ ስብሰባዎችን እስከማቋረጥ የደረሰ ሲሆን፣ ለዚህ ምክንያቱ በሀገሪቱ እየተቀጣጠለ ያለውና መቋጫ ሊገኝለት ያልቻለው ሕዝባዊ አመጽና ግድያ እንደሆነ ታውቋል።
በተለይ ባለፈው ሳምንት የ ኦሮሞ ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት -(ኦ ህ ዴድ ) እና የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ብአዴን) አባላት የሆኑ የምክር ቤት እንደራሴዎች እጅግ አሣሳቢ ደረጃ ላይ በደረሰው በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለምናነሳቸው ጥያቄዎች አቶ ኃይለማርያም በአካል ተገኝተው ምላሽ ካልሰጡ ከእንግዲህ አንሰበሰብም በማለት በማደማቸው ስብሰባው ጠቅላላ ተቋርጧል።
ይህን ተከትሎ አቶ ኃይለማርያም በትናንትናው ዕለት የፓርላማ አባላቱን በዝግ ስብሰባ ያነጋገሩ ሲሆን፣ ለሦስት ሰዓታት የዘለቀው ይህ ስብሰባ ለታማኝ መገናኛ ብዙሀን ሳይቀር በመከልከሉ አባላቱ በምን ጉዳይ ላይ እንደተነጋገሩ ለማወቅ አልተቻለም።
በአካባቢው ከፍተኛ የደህንነት ጥበቃ የተደረገ መሆኑን፣ ሁሉም ተሰብሳቢዎች ማንኛውንም አይነት የአሌክትሮኒክስ እቃዎችን ውጭ አስቀምጠው እንዲገቡ መደረጉንና አጠቃላይ ፍተሻው ከዚህ በፊት ከነበሩት ሁሉ ከፍተኛ እንደነበር ታውቛል።

No comments:

Post a Comment