Sunday, December 3, 2017

ወልድያ ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀስቅሷል

የመቀሌ የእግር ኳስ ቡድን በአጋዚ ወታደሮች ታጅቦ ወደ ወልዲያ ከተማ መግባቱን ተከትሎ የተነሳው ተቃውሞ እስከምሽት ድረስ በመዝለቅ ተባብሶ መቀጠሉን ለማወቅ ተችሏል። የህወሀት መንግስት ደጋፊ በሆኑ ግለሰቦች ንብረቶች ላይ ህዝቡ እርምጃ በመውሰድ ላይ ሲሆን በርካታ የንግድ ቤቶች ተቃጥለዋል። መስታወታቸው ተሰባብሯል። የአጋዚ ሰራዊትና የአማራ ልዩ ሃይል ህዝቡ ላይ በመተኮስ ላይ ሲሆኑ የተገደሉ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ እየተነገረ ነው። ተቃውሞው ወደሌሎች አከባቢዎችም ዘልቋል። በቆቦ በርካታ ተሽከርካሪዎች ተሰባብረዋል።
በወልድያ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የሞቱ ሰዎች መኖራቸውን መረጃ ደርሶናል። ቆቦ ላይ መኪኖች መሰባበራቸውም ተሰምቷል። ተቃውሞውም ወደ ወልድያ ዩንቨርስቲ ተስፋፍቷል።ጎንደር በር ላይ የሚገኘው አቢሲኒያ ባንክ ያለበት ህንፃን ጨምሮ በርካታ ህንጻዎች ተሰብራርዋል። የአጋዚ ወታደሮች ከተማውን ወረዋል።

No comments:

Post a Comment