Tuesday, December 19, 2017

እንግሊዝ ፍርድ ቤት የአርበኞች ግንቦት7 የአመራር አባል የሆኑትን ዶ/ር ታደሰ ብሩን ከቀረበባቸው የሽብር ክስ ነጻ አላቸው።

ዶ/ር ታደሰ በእንግሊዝ መንግስት 8 ያክል ክሶች ቀርበውባቸው ነበር። ለወራት ከአገር እንዳይወጡ ታግደው ጉዳያቸውን ሲከታተሉት የቆዩት ዶ/ር ታደሰ፣ እርሳቸውና ጠበቆቻቸው ባቀረቡዋቸው የመከላከያ ማስረጃዎች ከሁሉም ክሶች ነጻ ተብለዋል።
ዶ/ር ታደሰ ብሩ ውሳኔው ለአገራቸው ነጻነት ለሚታገሉት ሃይሎች ሁሉ የምስራች መሆኑን ተናግረዋል።
የዶ/ር ታደሰ የትግል አጋር እና የአርበኞች ግንቦት7 ሊቀ/መንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ በአጭር ጊዜ የተሰጠው ውሳኔ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል። 
ውሳኔው የትግላቸውን ትክክለኛነትና ለምን አላማ እንደሚታገሉ ያሳዬበት መሆኑን ፕ/ር ብርሃኑ ተናግረዋል ። 
የህወሃት ኢህአዴግ አገዛዝ በጅምር ላይ ያለውን መኖሪያ ቤትዎን ወርሶ በመሸጡ ምን እንደተሰማቸው የተጠየቁት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፣ ውሳኔውን በመገኛ ብዙሃን ሲሰሙ ከመሳቅ በስተቀር ምንም እንዳልተሰማቸው ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment