Friday, December 22, 2017

በሶማሊ እና ኦሮምያ ክልል አጎራባች በሚገኙ ከተሞች የሚገኙ ታጣቂዎች እንዲነሱ ትዕዛዝ ተላለፈ

የመከላከያ አዛዦች ባስተላለፉት ትእዛዝ በሁለቱ ክልሎች የድንበር ከተሞች ላይ የሚገኙ የሶማሊ እና የኦሮምያ ክልል ታጣቂዎች ከአካባቢው እንዲርቁ እና ከተሞቹ ሙሉ በሙሉ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ይውላሉ። ትዕዛዙን የማይፈጽሙ የሁለቱ ክልሎች ታጣቂዎች ትጥቃቸውን እንዲያወርዱ ተደርጎ እርምጃ ይወሰድባቸዋል ተብሎአል። ከኦሮምያ ክልል ከምስራቅ ሃረርጌ በኩል 8 ወረዳዎችን መከላከያ ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠራቸዋል። 
የኦሮምያ ክልል ታጣቂዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከአጋዚ ወታደሮች ጋር አለመግባባት እየፈጠሩ አልፎ አልፎም እርስ በርስ እየተታኮሶ ከሁለቱም ወገን የሰው ህይወት ሲጠፋ ቆይቷል። አቶ ለማ መገርሳ የኦሮምያ ታጣቂዎች ህዝቡን ከጥቃት እንዲከላከሉ አስፈላጊውን መስዋትነት እንዲከፍሉ በመገናኛ ብዙሃን ተናግረው ነበር። የአሁኑ ትዕዛዝ ለብዙ የኦሮምያ ክልል ባለስልጣናት የሚዋጥ አልሆነም። ህዝቡ መከላከያ ከክልሉ እንዲወጣ እየጠየቀ ባለበት በዚህ ሰአት መከላከያን በብዛት እያስገቡ ክልሉን እንዲቆጣጠር የማድረጉ እንቅስቃሴ ህዝቡን እያስቆጣው ነው።

No comments:

Post a Comment