Friday, January 29, 2016

በኢትዮጵያ በአዮዲን የበለጸገ ጨው የሚጠቀመው ህዝብ እጅግ ዝቅተኛ ነው ተባለ

ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያ በአዮዲን የበለጸገ ጨው የሚጠቀመው ህዝብ 23 በመቶ ያህል መሆኑን ከኢትዮጵያ የምግብ መድሀኒትና ፋርማሱዪቲካል ልማት ኢንስቲትዪት የተገኘ ጥናት አመልክቷል።
አብዛኛው ህዝብ በአዮዲን የበለፀገ ጨው ማግኘት ባለመቻሉ የእንቅርት በሽታን ጨምሮ የህጻናት አእምሮና እድገት ዝግመትን፣ ነፍሰጡር ሴቶች ላይ ውርጃንና የመሳሰሉ ችግሮችን በማስከተል ላይ ይገኛል።
መንግስት ቁጥሩን ወደ 70 በመቶ ለማሳደግ እየሰራሁ ነው ብሎአል። በአሁኑ ወቅት በአዮዲን የበለፀገ የጨው ማምረቻ ፋብሪካ በ220 ሚሊየን ብር በአፍዴራ ለመገንባት የታቀደ ቢሆንም የፋይናንስ ችግር መኖሩ ግን እቅዱ በቅርቡ እንዳይተገበር እንቅፋት ሊሆን ይችላል ተብሎአል።
በአዮዲን የበለፀገ ጨው እጥረት ጋር በተያያዘ አብዛኛው የገጠር ህዝብ በእንቅርት ህመም እንደሚሰቃይ ጥናቱ ይጠቁማል።

No comments:

Post a Comment