Monday, January 11, 2016

ኢትዮጵያ በተመድ የልማት ፕሮግራም መስፈረት የ174ኛ ደረጃን ያዘች

ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት የልማት ፕሮግራም UNDP ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያ ከ188 የአለም አገራት 174ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ገልጿል። ድርጅቱ የኢኮኖሚ እድገትን፣ ልማትን፣ የጸጥታ ጉዳዮችን ፣ የፖለቲካ ነጻነትንና ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮችን በማጥናት የሚያወጣው ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ ካለፈው አመት ከነበረችበት ደረጃ ዘንድሮ አንድ ደረጃ ዝቅ ብላለች። በአለማ ላይ ካሉት አገራት ኢትዮጵያ መብለጥ የቻለችው 14 አገራትን ብቻ ሲሆን፣ ሁሉም በአፍሪካ የሚገኙ ናቸው።

ምንም እንኳ ገዢው ፓርቲ ሁለተንተናዊ እድገት እንዳሳየ በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙሃን ቢገልጽም፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግን ኢትዮጵያን በአለም መጨረሻ ከሚሰለፉ አገራት ተርታ አስቀምጧታል።
በሰው ልማት ሃብታቸው ከ1-5 ያለውን ደረጃ የያዙት ኖርዌይ፣ አውስትራሊያ፣ ስዊዘርላንድ፣ ዴንማርክና ኔዘርላንድስ ናቸው።

No comments:

Post a Comment