Tuesday, January 19, 2016

ለኪሳራ የተዳረጉ መለስተኛ ፋብሪካዎች ሰራተኞችን መቀነስ ጀመሩ

ጥር ፲ (አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኤሌክትሪክ ሀይል መቆራረጥ ችግር እጅግ ተባብሶ ከመቀጠሉ ጋር ተያይዞ በተለይ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ተቁዋማት ለከፍተኛ ኪሳራ እየተዳረጉ፣ ሰራተኞችም እየቀነሱ ነው።
የሃይል እጥረቱ ተባብሶ በአሁኑ ወቅት በእየለቱ ቢያንስ ለግማሽ ቀን ወደመጥፋት ደረጃ ተሸጋግሯል። ት/ቤቶች፣ሆስፒታሎች ፣ዳቦ ቤቶችና የመሳሰሉ ስራቸው እየተስተጉዋጎለ ሲሆን አምራች ተቁዋማት ሰራተኞችን እየቀነሱ ነው።
አንድ በዳቦ መጋገር ስራ የተሰማሩ ባለሀብት ሀይል ተቋርጦ የሚመጣበት ጊዜ የማይታወቅ በመሆኑ ምርት ለመቀነስ መገደዳቸውን፣ እንዲሁም ከዚህ ቀደም ከነበሩዋቸው 10 ያህል ሰራተኞች ግማሽ ያህሉን ለማሰናበት መገደዳቸውን ገልጸዋል።ችግሩ በዚሁ ከቀጠለ ስራውን አቆማለሁ ብለዋል። አንዳንድ የፋብሪካ ውጤቶችም ባልተጠበቀ ሁኔታ የመሸጫ ዋጋቸው ላይ ጭማሪ እያሳዩ መሆኑ አስደንጋጭ ሆኖአል።
መንግስት በግልጽ በሚታይ ሁኔታ የሃይል እጥረት ቢያጋጥመውም አሁንም እንደ ጅቡቲ ላሉ ጎረቤት ሀገራት በርካሽ ዋጋ ሀይል መሸጡን ቀጥሎበታል።

No comments:

Post a Comment