Friday, January 8, 2016

እነ ሀብታሙ አያሌው ለጥር 10/2008 ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

አቃቤ ህግ በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብርተኝነት ክስ መስርቶባቸው በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ ተበይኖላ...ቸው አቃቤ ህግ ለጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ጠይቆባቸው ጉዳያቸውን በእስር ላይ ሆነው እየተከታተሉ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች በድጋሜ ለጥር 10/2008 ዓ.ም ተቀጥረዋል፡፡
ዛሬ ታህሳስ 29/2008 ዓ.ም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በእነ ሀብታሙ አያሌው ላይ የተጠየቀው ይግባኝ ላይ ብይን ይሰጣል ተብሎ ቢጠበቅም ዳኛ ዳኜ መላኩ ‹‹የምንመረምረው ነገር አለ›› በሚል ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡
ይግባኝ የተጠየቀባቸው ተከሳሾች ሀብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ፣ ዳንኤል ሺበሺ እና አብርሃም ሰለሞን ሲሆን፣ ሁሉም ተከሳሾች ነሀሴ 14/2007 ዓ.ም በስር ፍ/ቤት ነጻ ቢባሉም እስካሁን በእስር ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡

No comments:

Post a Comment