Thursday, January 14, 2016

የወጣቱ የህሊናና የፓለቲካ እስረኛ የሃብታሙ ሃብታሙ አያሌው መልእክት ‪#‎ከቂሊንጦ_እስር_ቤት‬።

እኔ ተስፋ አረጋለሁ ህዝብ ተሸንፎ አያውቅም።

እኔ ፅኑ እምነት አለኝ በመጨረሻ ህዝብ ያሸንፋል።
እዚህ የተገኝነው ብቸኛ አማራጭ በሆነው የሰላማዊ ተግል ሜዳ ላይ ተገኝተን ነው ለዚህ ግፍ የተዳረግነው።የመረጥነው ትግል ሌላ ቢሆን ኖሮ እዚህ አንገኝም ነበር። ይሁንና እኛ እዚህ እየከፈልን ያለነው መከራ በአሁኑ ሰአት እየተገደለ ካለውና…በርሃብ አለንጋ ከሚገረፈው ወገናችን አይበለጥብንም። ስለዚህ አሁንም በሰላማዊ መንገድ ትግሉ ይቀጥል ።
መቼም በየትኛውም ቦታ
በታሪክ ህዝብ ተሸንፎ አያውቅም በርቱ ድል የህዝብ ነው ብሎል። በመጨረሻም ሃብታሙ አያሌው በአሁኑ ሰአት በኩላሊት ህመም የሚሰቃይ ሲሆን ህክምናውን የሚከታተልበት የዘውዲቱ ሆስፒታል ህመሙ አሳሳቢ
የነበረ በመሆኑ ተኝቶ እንዲታከም የወሰነ ቢሆንም በወቅቱ ወህይኔ ቤቱ በመከልከሉ ተኝቶ ሳይታከም መቅረቱን አጫውቶኛል። በዚሁ በቂሊንጦ እስር ቤት የቀድም የአንድነት ለዲምክራሲና ለፍትህ ፓርቲ
አንድነት አባለት አዲስ አበባና ሰሜን ጎንደር አባላት አሉ እስማኤል ዳወድ አባይ ዘውዱ ሰሜን ጌንደር በጠና ተም መድሃኒት በማጣት የተሰቃየ በመጨረሻም የሃብታሙ አያሌው ባለቤት ወ/ ሮ ቤቴልሄም ሰው አስቸግራ ገዝታ በመስጠት ከፈጣሪ ጋር ህይወቱን ታድገዋለች ። አንጋው ከሰሜን
ጎንደር ይገኛል ። በአጠቃላይ ሃብታሙ አያሌው ከተያዘበት እለት ጀምሮ እስከዛሪዋ እለት
የነበረውን አጠቃላይ ሁኔታ በሚያስገርም አገላለፅ ያለማቆረጥ ለ2:00 ሰአት አጫውቶኛል ዝርዝር ሁኔታን ከምስል ጋር አደርሳለው። በመጨረሻም እስረኞቹን ለመጠየቅ አስፈላጊ ነገሮችን ላምሉልን ለቀድም የፈረንሳይ ለጋሲዮን አንድነት አባላቶች ለወንድማችን ናቴ ባለቤት ለዘወትርተባባሪዋ ፍቅርተና ተብብር ላደረጉ ሁሉ ልባዊ ምስጋና ይድረሳችሁ።ድል
የህዝብ ነው።

No comments:

Post a Comment