Friday, January 8, 2016

በኒውዚላንድ የሚኖሩ ሴቶች ገንዘብ አሰባስበው ለአርበኞች ግንቦት7 ለገሱ

ታኀሳስ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኒዉዚላንድ ዌሊንግቶን የሚኖሩ ሴቶች ፣ በበረሃ ውስጥ ያሉ ሴቶችን ለመርዳት በሚል ተነሳስተው ለአርበኞች ግንቦት ሰባት የሴት ታጋዮች ፍጆታ የሚዉል ገንዘብ መለገሳቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመልክቷል።
ሴቶቹ ይህ ጅማሪ እንጂ የመጨረሻዉ እንደማይሆን፣ ለወደፊቱ ራሳቸዉን በማደራጀት ቀጣይ የሆነ እርዳታ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
በገና በዓል ቀን ሴት እሕቶቻችን በጫካ ለኛ ነፃነት ሲታገሉ እኛ የተመቻቸ አገር ላይ ሆነን ቢያንስ አስበናቸዉ ልንዉል ይገባል በማለት ድጋፍ ለማድረግ መነሳሳታቸውንም አክለዋል።

No comments:

Post a Comment