Wednesday, January 20, 2016

ለቤተ እስራኤላዊያን ማቋቋሚያ ልዩ በጀት ተመደበላቸው

ጥር ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የእስራኤል መንግስት በአገሩ ውስጥ ለሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ቤተእስራኤላዊያን ማኅበረሰብ አባላት ማቋቋሚያ ይሆን ዘን 55 ሚሊዮን የእስራኤል ሻክል መመደቡን አስታውቋል።
ቁጥራቸው ከ 3 ሽህ 600 በላይ የሚሆኑት ቤተ-እስራኤላዊያን ከተቀረው የእስራኤል ማኅበረሰብ ጋር የውህደት መስተጋብር ያደርጉ ዘንድ ያስችላል የተባለውን ውሳኔ የአገሪቱ ፓርላማ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል።
የቤተ እስራኤላዊያንን አቅም በመገንባት በትምህርትና በሥራ መስክ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማጎልበት ይረዳል የተባለው መርኅግብርን ለማስፈፀም አራት ዓመታት ሊፈጅ እንደሚችል የገንዘብ ሚንስቴሩ አስታውቀዋል ሲል ጄሩሳሌም ፖስት ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment