Friday, January 29, 2016

በጋምቤላ በቀጠለው ግጭት 7 ሰዎች ተገደሉ

ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል ዳይሬክተር አቶ ኒካው ኦቻላ ለኢሳት እንደገለጹት የንዌር ተወላጆች የጋምቤላ እስር ቤትን ሰብረው በመግባት 7 የአኝዋክ ተወላጆችን ሲገድሉ፣ 7ቱን ደግሞ አቁስለዋል። 4 የሌሎች ብሄረሰቦች አባላት መቁሰላቸውምን ዳይሬክትሩ ገልጸዋል።
በሁለቱ ብሄረሰቦች መካካል እንዲህ አይነት ደም የሚያፋሰስ የመረረ ግጭት ተቀስቅሶ እንደማያውቅ የገለጹት አቶ ኒካው፣ ለአሁኑ ግጭት መባባስ የሪክ ማቻር ወታደሮችንና ከደቡብ ሱዳን የተሰደዱ ንዌሮችን ተጠያቂ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት የሚያስታጥቃቸው የሪክ ማቻር ወታደሮች መሳሪያ እንደልባቸው በማግኘታቸው ጥቃት እየፈጸሙ ነው የሚሉት ዳይሬክተሩ፣ ብዙዎቹ የደቡብ ሱዳንን ግጭት እየሸሹ የሚመጡት የሪክ ማቻር ደጋፊዎች ኑዌሮች በመሆናቸውን ችግሩን አባብሶታል ብለዋል። የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት በከተማው ቢሰማሩም ግጭቱን ሊቆጣጠሩት አልቻሉም።
በከተማዋ የሚገኙ መንገዶች ፣ ትምህርት ቤቶችና ባንኮችን የመሳሰሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተዘግተው መዋላቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment