Wednesday, October 7, 2015

በጎንደር የፌደራል ፖሊስ አንድ የመዋለ ህጻናት ወስዶ አልመልስም አለ

መስከረም ፳፮ (ኅያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነዋሪዎች እንደገለጹት በከተማው ቀበሌ 9 የድሃ ልጆች የሚማሩበትን መዋለ ህጻናት ትምህርት ቤት፣ ምርጫውን ሰበብ ተደርጎ ለፌደራል ፖሊስ በጊዜያዊነት ከተሰጠ በሁዋላ፣ ፖሊስ አለቅም በማለቱ ከነዋሪዎች ጋር ውዝግብ ተፈጥሯል። ፖሊስ በ15 ቀናት ቦታውን እንደሚለቅ ገልጾ፣ ትምህርት ቤቱን ቢረከብም፣ እስካሁን ድረስ ባለመልቀቁ ወላጆች ልጆቻቸውን ማስተማር አልቻሉም። ወላጆች አቤቱታ ለማቅርብ ብንሄድም በፖሊሶች ተደብድበናል በማለት ገልጸው፣ በዚህም የተነሳ አቤቱታችንን የሚቀበለን አጥተናል ብለዋል። ጉዳዩን በማስመልከት ለወረዳው ባለስልጣናት ስልክ ብንደውልም ልናገኛቸው አልቻልም።

No comments:

Post a Comment