Thursday, October 8, 2015

በዲላ ከተማ መብራት በመጥፋት ነዋሪዎች ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናገሩ

መስከረም ፳፯ (ኅያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት 4 ቀናት ያለማስጠንቀቂያ የተቋረጠው ኤሌክትሪክ፣ በንግድ ቤቶች እና በነዋሪዎች የእለት ተለት ህይወት ላይ ችግር ማስከተሉን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የኤሌክትሪክ አገልግሎቱ የተቋረጠበት መንስኤ ለህዝቡ አለመገለጹንም ተናግረወዋል። ከዚህ በፊት በከተማው በተደጋጋሚ የ ኤሌክትሪክ መቋረጥ የሚከሰት ሲሆን ፣ ያሁኑ ደግሞ የተለየ ነው ሲሉ ነዋሪዎች በምሬት ይገልጻሉ።
በከተማው በሳምንት አንድ ቀን ይቀርብ የነበረው የውሃ ስርጭትም ከተቋረጠ ሳምንታትን አስቆጥሯል፡፡
በከተማዋ በየመንገዱ ለውሃ መያዣነት የተደረደሩ ባዶ ቢጫ የዘይት ጄሪካኖች ዲላን ቢጫዋ ከተማ የሚል ስያሜ አሰጥቷታል።

No comments:

Post a Comment