Friday, October 9, 2015

በ በቆጂ በተነሳው ተቃውሞ ብዙ ወጣቶች ታሰሩ

መስከረም ፳፰ (ኅያ ስምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በ በቆጂ ከተማ ከቤት ማፍረስ ጋር በተያያዘ በተነሳ ተቃውሞ ከ20 በላይ ወጣቶች በፖሊሶች ተደብድበው ሆስፒታል የገቡ ሲሆን፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ነዋሪዎች ደግሞ ተደብድበዋል።

ግጭቱ የተከሰተው የወረዳው ባለስልጣናት ቤት አፍራሽ መኪኖችን በመላክ ህገወጥ ቤቶች ያሉዋቸውን ቤቶች ማፍረስ መጀመራቸውን ተከትሎ ሲሆን፣ ነዋሪዎች ድንጋይ በመወርወር ተቃውሞቸውን ገልጸዋል። አንድ የፖሊስ መኪናም በድንጋይ ተመታለች።
የመንግስት ባለስልጣናት በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን የማፍረስ እቅድ ይዘዋል።

No comments:

Post a Comment