Wednesday, October 14, 2015

በሲዳማ ዞን በተነሳ ግጭት ጉዳት እየደረሰ ነው

ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በሲዳማ ዞን በማልጋ ወረዳ ፣ ወታራና ጉጉማ በሚባሉ አካባቢዎች ከ2004 ዓም ጀምሮ በእየአመቱ የሚቀሰቀሰው ግጭት ሰሞኑን አገርሽቶ፣ እስካሁን 2 ሰዎች በከባድ ሁኔታ ተጎድተው አዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ሲገቡ፣ መጠኑ ያልታወቀ ንብረትም ወድሟል። በቦንኬ ጎሳና በጉኑፋ ጎሳዎች መካከል የተነሳው ግጭት መንስኤ የአንዱ አካባቢ ተወላጅ ሌላውን ማስተዳደር አይችልም የሚል ሲሆን፣ የአካባቢው ተቃዋሚች በበኩላቸው ግጭቱ የዘር ፖለቲካው ውጤት ነው ይላሉ። ግጭቱን ለማርገን የደቡብ ክልል ልዩ ሃይል አባላት ወደ አካባቢው ተንቀሳቅሰዋል።

በአካባቢው የሚከሰተውን ግጭት ለማብረድ በሚል በየአመቱ 8 ሚሊዮን ብር በጀት እንደሚያዝ የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ ችግሩ ሳይፈታ ገንዘቡ ግን ወጪ መደረጉ እንደሚገለጽ ይናገራሉ።

No comments:

Post a Comment