Thursday, October 8, 2015

በሳዑዲ በሃጂ ስነ-ስርዓት ላይ የሞቱ ኢትዮጵያውያን በሀገር አቀፍ ደረጃ አለመታሰባቸው ሙስሊሞችን አሳዝኗል

መስከረም ፳፯ (ኅያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሁለት ሳምንት በፊት በሳዑዲ አረቢያ ሚና አካባቢ በሀጂ ስነ-ስርዓት ወቅት በተከሰት ግፊያና መጨናነቅ በደረሰ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያዊያን ቁጥራቸው ከ47 በላይ የበለጠ ቢሆንም ፣ የኢህአዴግ መንግስት ለዚህ ከባድ ሐዘን የሰጠው ትኩረት ማነስ እንዳሳዘናቸው ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው በአዲስአበባ የሚኖሩ ሙስሊሞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመጅሊሱን ወሬ በመያዝ ለሞቱት ወገኖች መጽናናትን ይመኛል ከማለት በዘለለ በመንግስት በኩል አደጋውን አስመልክቶ ምንም የተባለ ነገር አለመኖሩ ሕዝበ ሙስሊሙን እንደመናቅ ይቆጠራል ብለዋል፡፡
ሙስሊም ማህበረሰብ ከባድ ሐዘን ላይ ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ ድንገተኛ አደጋው በመንግስ በኩል ተገቢውን ትኩረት አለማግኘቱ እንዳሳዘናቸው ይገልጻሉ።
በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትም የወገኖቻችን ሐዘን ሀገር አቀፍ ገጽታ ባለው መልኩእንዲታሰብ ያደረገው ነገር አለመኖሩም ወኪልነቱን ጥያቄ ውስጥ የሚጥል ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡

No comments:

Post a Comment