Wednesday, October 7, 2015

‪#‎የጋሙ‬ ጎፋ የላ ሳውላ ገበሬዎች ማዳበሪያ እንዲገዙ እየተገደዱ መሆናቸው ታወቀ፡፡


(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
‪#‎የጋሙ‬ ጎፋ የላ ሳውላ ገበሬዎች ማዳበሪያ እንዲገዙ እየተገደዱ መሆናቸው ታወቀ፡፡
‪#‎የላይ‬ አርማጭሆ ገበሬዎች በህወሓት አገዛዝ ፌደራልና ልዩ ኃይል ፖሊሶች በገፍ እየታፈሱ ወደ እስር ቤት እየተጋዙ ነው፡፡
‪#‎በጎንደር‬ ከተማ የተጀመረው ወጣቶችን የማሰር ዘመቻ አሁንም ተባብሶ መቀጠሉን የአርበኞች ግንቦት 7 ዜና ምንጮች የላኩልን መረጃ አመለከተ፡፡

የጋሙ ጎፋ የላ ሳውላ ገበሬዎች ማዳበሪያ እንዲገዙ እየተገደዱ መሆናቸው ታወቀ፡፡
ማዳበሪያ በግዴታ እንዲገዙ በአገዛዙ ካድሬዎች ጫና እየተደረገባቸው የሚገኙት ገበሬዎች እጅግ በጣም አነስተኛ የእርሻ ማሳ እና ለም መሬት ያላቸው ናቸው፡፡
ገበሬዎቹ ከአገዛዙ ካድሬዎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ "ወትሮ በየግል ቤታችን ውስጥ አንድ በሬ አርደን እንበላ ነበር አሁን እናንተ ከመጣችሁብን ወዲህ ግን አንድ መደብ ስጋ ለአራት እንኳ እያረረብን ይገኛል፡፡ እንዲህ ከምታሰቃዩን እባካችሁ ግደሉን እና እርፍ እንበል..." በማለት በህወሓት አገዛዝ ላይ ያላቸውን ምሬት ገልፀዋል፡፡
በተያያዘ ዜናም የህወሓት አገዛዝ ለህዝቡ ወገንተኝነት ያሳያሉ ብሎ ያመነባቸውን የጋሙ ጎፋ ዞንና ልዩ ልዩ ወረዳዎችን ባለስልጣናትን ከሹመታቸው ሽሮ አባሯቸዋል፡፡
ከተባረሩት መካከል አቶ ጌኞ የተባለው የጨንቻ ወረዳ አስተዳደሪ፣ የከምባ ወረዳ አስተዳዳሪ እና የዞኑ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ይገኙበታል፡፡


ምንም እንኳን በአካባቢው ህዝብ ዘንድ የተጠሉ ቢሆኑም ቅሉ የጋሙ ጎፋ ዞን አስተዳደሪ የሆነውን ጥላሁን ታደሰ፣ በዞኑ የድርጅቱ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ ተስፋዬ ቤልጅግንና ሌሎችን ለጊዜው ስማቸው ያልታወቀውን የዞንና የወረዳ ባለስልጣናት አገዛዙ ከሹመታቸው የመሻርና የማባረር ዕቅድ እንዳለው ታውቋል፡፡
የላይ አርማጭሆ ገበሬዎች በህወሓት አገዛዝ ፌደራልና ልዩ ኃይል ፖሊሶች በገፍ እየታፈሱ ወደ እስር ቤት እየተጋዙ ነው፡፡
ዘረኛው እና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከልዩ ኃይል እና ከመከላከያ ተመርጦ የተውጣጣ ሰራዊት በላይ አርማጭሆ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ማለትም በሙሴ ባንብ በጃኒካው፣ በገንበራ እና በሌሎች በርካታ አካባቢዎች ያሰራጨ ሲሆን ከሦስቱ ክፍሎች የተጣመረው ኃይል በየገበሬው መንደር ተሰግስጎ በማሸበር በመሳሪያ ገፈፋና በአፈሳ ተግባራት ላይ በሰፊው ተሰማርቶ ይገኛል፡፡
በመሆኑም በላይ አርማጭሆ ገንበራ ቀበሌ ብቻ
• አቶ አራጋው አበራ(የሚሊሻ ኮማንደር የነበረ)
• አቶ አወቀ ጎሉ
• አቶ ተቀባ ብርሃን
• ወጣት ቴዎድሮስ ሙሉ
• ወንድሙ ሙሉ እና
• ወይዘሮ ደብሬ የኔዓለም የተባሉ ገበሬዎች ታፍነው ተወስደዋል፡፡
እነኚህን ስማቸው የተዘረዘሩትን ጥቂት ድሃ ገበሬዎች ጨምሮ በአገዛዙ የታጠቁ ኃይሎች በየቀኑ ከቀያቸው እየታፈኑ የሚወሰዱት ሰዎች በትክል ድንጋይ ልዩ ኃይል የጦር ካምፕ ውስጥ ታጉረው እደሚገኙ ተገልጿል፡፡
በጎንደር ከተማ የተጀመረው ወጣቶችን የማሰር ዘመቻ አሁንም ተባብሶ መቀጠሉን የአርበኞች ግንቦት 7 ዜና ምንጮች የላኩልን መረጃ አመለከተ፡፡
ባለፈው መስከረም 17 ቀን 2008 ዓ.ም የጎንደር ወጣቶች "የፈራ ይመለስ" የሚል ፅሁፍ ከፊትና ከጀርባ የታተሙባቸው ቀያይ ቲሸርቶች ለብሰው የመስቀልን በዓል ለማክበር ወደ አደባባይ ወጥተው ለአገዛዙ የተቃውሞ ድምፃቸውን በማሰማታቸው ነበር አፈሳውና እስሩ የጀመረው፡፡
አገዛዙ የፀጥታ ኃይሎችን በከተማዋ በማሰራጨት አሁንም ወጣቶችን እያፈሰ ወደ ወህኒ የማጋዙን ስራ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በጎንደር ከተማ እየተከናወነ በሚገኘው የወጣቶች አፈሳ በተለይም ደግሞ የቀበሌ 18 ወጣቶች በከፋ መልኩ የእስራቱ ሰለባ መሆናቸው ተዘግቧል፡፡
ጎንደር ቀበሌ 18 በመስጊድና ሸንኮራ ሆቴል አካባቢ በሚገኙ መዝናኛ ቤቶች ውስጥ የተገኙ ወጣቶች በፖሊሶች እየታፈሱ ሲወሰዱ መመልከታቸውን የዓይን እማኞች ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ተናግረዋል፡፡

No comments:

Post a Comment