Wednesday, October 14, 2015

በኢትዮ-ሱዳን ድንበር የተነሳው ጦርነት እንደቀጠለ ነው

ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው እሁድ ጀምሮ በኢትዮጵያውያንና በሱዳን መንግስት ወታደሮች መካከል የተነሳው ጦርነት መቀጠሉን ከአካባቢው የደረሱን መረጃዎች ያመለካታሉ።ኢትዮጵያውያን ታጣቂዎች፣ ከዚህ ቀደም ማንነታቸው ያልታወቁ የሱዳን ታጣቂዎች 8 ኢትዮጵያውያንን ለሹፌርነት እንቀጥራችሁዋለን በማለት በአሰቃቂ ሁኔታ ከመኪና ላይ አውርደው መግደላቸውን ተከትሎ፣ ኢትዮጵያውያኑ በወሰዱት አጸፋ እርምጃ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የሱዳን ወታደሮችን ገድለዋል።

የሱዳን መንግስት ተጨማሪ ሃይል ወደ አካባቢው ልኳል። የኢህአዴግ መንግስት በበኩሉ የመተማ ገላባትን ገበያ በመዝጋት ህዝቡ ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ማድረጉን የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ።
የሱዳን ባለስልጣናት ኢትዮጵያ ሰፊ የሆነ መሬት ይዛብናለች በማለት የድንበር ማካለሉ በፍጥነት እንዲያልቅ ጠይቀዋል። ሱዳኖች ከዚህ ቀደም በገዢው ፓርቲ ፈቃድ ሰፊ መሬት ቢሰጣቸውም፣ አሁንም ተጨማሪ መሬት መጠየቃቸው የአካባቢውን ነዋሪዎች እያስቆጣ፣ ለተደጋጋሚ ግጭት መንስኤ ሆኗል።

No comments:

Post a Comment