Wednesday, October 7, 2015

ጸረ ሙስና ወደ አንድ ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ከዝርፊያ ማዳኑን አስታወቀ

መስከረም ፳፮ (ኅያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ በማካሄድ ላይ ባለው 11ኛ ጉባኤ በተለያዩ ክልሎች ከ937 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳኑን ገልጿል።

ከክልሎች ሁሉ ከፍተኛ ገንዘብ ከስርቆት የዳነው በአማራ ክልል ነው ሲል አክሎ ጠቅሷል።
በዚህ ጊዜ እንደተገለጸው ግልጽነት በጎደለው የግዢ ሂደት ሊባክን የነበረ ከ937 ሚሊየን ብር በላይ የህዝብ ገንዘብ ለማዳን ተችሏል። ከሙስና ጋር በተያያዘ ከ3 ሺ በላይ የመንግስት ሰራተኞች መታሰራቸውንም ቢገልጽም፣ የሰራተኞችን የስልጣን ደረጃ አላመላከተም።
ጸረ ሙስና በአንድ አመት ውስጥ ይህን ያክል ገንዘብ ማዳኑን ከገለጸ፣ ሳያድነው የቀረው ገንዘብ ምን ያክል ሊሆነው ነው ሲል ዘጋቢያችን አስተያየቱን በጥያቄ አስፍሯል።
ጸረ ሙስና የባለስልጣናትን ሃብት ለህዝብ ይፋ ለማድረግ እንደማይፈልግ አስታውቋል። ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ልማቱን ለማስቀጠል ሲባል በሙስና እንደማይወነጀሉም ኮሚሽነሩ አሊ ሱሌይማን ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment