Thursday, October 8, 2015

የዞን 9 ጦማሪያን “ዳኞች ስልጠና ላይ ናቸው” በሚል ምክንያት ፍርድ ቤት ለ38ኛ ጊዜ ተቀጠሩ

መስከረም ፳፯ (ኅያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በነሶልያ ሽመልስ የክስ መዝገብ በሽብረተኝነት በተከሰሱት ወጣት ጸሃፍት ላይ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ሲጠበቅ ዳኞች “አዳማ ስልጠና ላይ ናቸው” በሚል ለ38 ኛ ጊዜ እንዲራዘም ተደርጓል።

ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት ለ5ኛ ጊዜ ቀጠሮ አራዝሟል። በአንድ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል የተወሰኑት መለቀቃቸው፣ ቀሪዎቹም ይለቀቃሉ የሚል ተስፋ አሳድሮ ነበር። ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ጸሃፊዎቹ እንዲፈቱ ጥያቄ አቅርቧል።

No comments:

Post a Comment