Tuesday, August 4, 2015

የጎሳ ፌዴራሊዝም፤ የአማራው ጎሳ የጅምላ መፈናቀልና አማራውን ለማጥፋት የሚደረገው ስልታዊ የወያኔ ትግሬዎች ዘመቻ – ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ

የትግራይ ብሄረተኞች እየሰሙ ያደጉት ሀሰተኛ የምድጃ ዳር ታሪክ በተመለከተ የሚከተለውን ለአንባቢ ላስተዋውቅ፤
ከዚህ በታች የተጠቀሰው የትግሬ ጎሰኝነት ያሳበደው እብዱ ውሻ ገብረ ኪዳን ደስታ የትግሬ ህዝብ በአማራ ላይ ለማነሳሳት እና ጥላቻን ለመፍጠር ሆን ብሎ ፈጥሮ የጻፈው የውሸት ታሪክ ያዘለ መርዝ መጽሐፍ ፣/ስንቱ ኢትዮጵያዊ አንብቦት ይሆን?/
keqeyachew yetefenakelu Amhara enatoch
“በዚያ ቀን የሸዋ ሰራዊት መቀሌን ሙሉ በሙሉ ዘረፈው፤ በአካባቢው የነበሩ መንደሮችም በሙሉ ተዘረፉ። እንደርታም እንዳልነበረች ሆነች። በየመንገዱ ትልቅ ትንሽ ህፃን ሳይሉ ሰለቡት። ቀጥሎም የምንሊክ ሰራዊት እንደርታን አወደማት። እንዳልነበረች ሆነች። ብቻ የወንድ ልጅ ይሁን እንጂ የተገኘ ሰው ሁሉ ይገደላል። የእንደርታ ሰዎችም ቢሆኑ ዝም ብለው አልታረዱም። በየቋጥኙና በየጫካው እየተደበቁ የምንሊክን ሰራዊት ሲፋለሙት ነበር። የምንሊክ ሰራዊት የመግደልና የመስለብ ሱስ ያለበት ነው።
ሰዎችን በገደለና በሰለበ ቁጥር ይፎክራል። ሌላው ይቅርና በመላ ኢትዮጵያ የተከበረውን የአብርሃ ወአጽብሃ ገዳምም እንዳለ ዘርፈውታል[ii]”። (ምንጭ፤ ገብረ ኪዳን ደስታ “የትግራይ ህዝብና የትምክህተኞች ሴራ ከትላንት እስከ ዛሬ” በሚለው መጽሃፉ ውስጥ ከጠቀሰው “ታሪክ ኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ በትግርኛ ቋንቋ ከታተመው መጽሃፍ የተጠቀሰ።
ስለ አማራ ህዝብና ስለ እነ ዐጼ ምንሊክ፤ ዐጼ ሃይለስላሴ ወዘተ በወላጆቻቸው ጥላቻን እየተጋቱ ያደጉት የዛሬዎቹ የወያኔ መንግስት መሪዎች ከልጅነት ጀምሮ ጥርሳቸውን ሰብረው ያደጉበትን በምድጃ ዳር የተማሩትን የጥላቻና የውሸት ታሪክ ከዘመናዊ የብሄረተኛነት አስተሳሰብ ጋር አዳቅለው አክራሪውንና ዛሬ ኢትዮጵያን እያፈረሰ ያለውን የትግራይ ብሄረተኛነት በማቀንቀን ኮትኩተው አሳደጉ። ዛሬ የትግራይ ብሄረተኛነት ጥቂቶች የሚጋሩት እብደት ሳይሆን እንደ ጀርመኑ የናዚ ወይም እንደ ጣልያኑ የፋሽዝም ርዕዮተ ዓለም በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የጎሳ ተወላጆቹን አስተሳሰብ በመቀየርና ከሰውነት ደረጃ በማውጣት የወያኔ ትግሬዎች ከትግሬ ጎሳ ውጭ ያለውን ኢትዮጵያዊ በተለይ ደግሞ የታሪክ ደመኛችን ነው የሚሉትን የአማራን ህዝብ እንደ አደገኛ አውሬ የሚያዩበትና የዚህንም ህዝብ ህልውና ጨርሰው ለማጥፋት የተነሱበት ደረጃ ላይ አድርሶአቸዋል። የትግሬዎች አካላዊ ገጽታ፤ መልክ፤ ባህልና ታሪክ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር መመሳሰል ሌላው ኢትዮጵያዊ የወያኔ ትግሬዎችን እንደ እራሱ ወገን እንጂ ለኢትዮጵያና ትግርኛ ተናጋሪ ላልሆኑ ኢትዮጵያውያን ይህን ያህል ጥላቻ ያላቸው ወገኞች ናቸው ብሎ እንዳይገምት አድርጎታል፤ አዘናግቶታልም። ስለዚህም የኢትጵዮጵያ ህዝብ የወያኔ ትግሬዎችን እዚህ ደረጃ ላይ ሳይደርሱና ብዙ ጥፋት ሳያደርሱ ሊያቆማቸው የሚችልበት ብዙ አጋጣሚዎች አልፈውታል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በሀገራችን በህዝቡ ዘንድ ቀርቶ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነን በሚሉት ዘንድ ስለ ጎሳ ብሄረተኛነት (ethnic nationalism) ያለው ግንዛቤ እጅግ የሚያሳዝን በመሆኑ ዛሬ ወያኔ እያደረሰ ያለውን የጎሳ ጽዳትና ጎሳን መሰረት የጅምላ ፍጅት ይከሰታል ብለው ለማሰብ አልቻሉም። በኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ ውስጥ ያንድ የኢትዮጵያ ጎሳ አባሎች (ትግሬዎች) የመንግስት ስልጣን ይዘው አንተ ይኸ ክልልህ ስላልሆነ ከዚህ ለቀህ ውጣ በማለት የሌሎችን ጎሳ አባላት (አማራን፤ አፋርን፤ አኑዋኮችን ወዘተ) እንደ አውሬ በጦር መሳሪያ የሚያሳደዱበትን፤ ህጻናትና አሮጊቶች ሽማግሌዎችና አቅመ ደካማዎችን ለሞትና ለዘግናኝ ስቃይ የሚዳርጉበት ዘመን ታይቶ አይታወቅም።

No comments:

Post a Comment