Monday, August 10, 2015

ሠማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ሊያካሂድ ነው አዲስ አመራር መራር ይመረጣል

ሰማያዊ ፓርቲ የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባኤ ነሐሴ 16 እና 17 የሚያካሂድ ሲሆን በዚህ ጉባኤ አዲስ መራር ይመረጣል
ተብሎም ይጠበቃል፡፡ በፓርቲው ህገ ደንብ መሰረት ጠቅላላ… ጉባኤ የሚደረገው በየ3 ዓመቱ መሆኑን የጠቀሱት የፓርቲው
ብሄራዊ ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰይድ ኢብራሂም፤ ጉባኤው በሐምሌ መካሄድ የነበረበት ቢሆንም በአንዳንድ ምክንያቶች
ምክር ቤቱ ለ3 ወር የማራዘም ስልጣኑን ተጠቅሞ እስከ ነሐሴ ማራዘሙን ገልፀዋል፡፡ በጉባኤው ላይ የሚሳተፉ አባላት ቁጥርና
የጉባኤውን አካሄድ ለመወሰን ብሄራዊ ምክር ቤቱ በነገው እለት ስብሰባ እንደሚያደርግም ሰብሳቢው ተናግረዋል፡፡ ጠቅላላ
ጉባኤውን እንዲያሳልጥ የተቋቋመው ኮሚቴም በእለቱ ሪፖርቱን ያቀርባል ብለዋል፡፡ በፓርቲው ህገ ደንብ መሰረት አንድ
ፕሬዚዳንት ለሁለት የስልጣን ዘመን ብቻ መመረጥ እንደሚችል የጠቆሙት አቶ ሰይድ፤ በአሁኑ ወቅት ፓርቲውን የሚመሩት ኢ/ር
ይልቃል ጌትነት ለሁለተኛ ጊዜ ይወዳደሩ አይወዳደሩ እስካሁን እንዳላሳወቁ ተናግረዋል፡፡

No comments:

Post a Comment