Thursday, August 20, 2015

የህወሓት አገዛዝ የደህንነት ቢሮ ጮርቃ ህፃናትን በሰላይነት እያሰለጠነ እንደሚገኝ ታወቀ

የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት
የህወሓት አገዛዝ የደህንነት ቢሮ ጮርቃ ህፃናትን በሰላይነት እያሰለጠነ እንደሚገኝ ታወቀ፡፡
የህወሓት ብሄራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ በርካታ ህፃናትን ከየአካባቢው መልምሎ አዲስ አበባ ውስጥ የስለላ ትምህርት በስውር እያስተማረ ይገኛል፡፡
ብሄራዊ መረጃና ደህንነት ህፃናቱን አገዛዙን ብቻ በታማኝነት እንዲያገለግሉ የሚያመቻች የስለላና ሌሎች ተያያዥ ትምህርቶችን ለረጅም ጊዜ በተከታታይ በመስጠት አስተሳሰባቸውን በመግራት አእምሯቸውን በሚፈለገው መልኩ ለመቅረፅ በከፍተኛ ሁኔታና በትኩረት ሲሰራበት ከርሟል፡፡
በብሄራዊ መረጃና ደህንነት ተመልምለው የስለላ ትምህርት ሲሰጣቸው የቆዩት ጮርቃ ህፃናት ስልጠናቸውን በቅርቡ ጨርሰው አገዛዙ ክትትል ማድረግ ወደሚፈልግባቸው የሲቪል ሰርቪስና ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲሁም ንግድ በሚካሄድባቸው ቦታዎች በሰላይነት እንዲሰማሩ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት የውስጥ ምንጮቻችን የደረሰን መረጃ ይገልፃል፡፡

No comments:

Post a Comment