Monday, August 24, 2015

ለመለስ አካዳሚ ግንባታ ተብሎ የተሰበሰበው ገንዘብ ለኢህአዴግ ፓርቲዎች ተከፋፈለ

ነኅሴ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አርሶአደሩ ፣ የመንግስት ሰራተኛውና ነጋዴው ለቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አካዳሚ ግንባታ በሚል በግዴታ ከ50 ብር ጀምሮ እንዲከፍል ቢደርግም፣ ምክንያቱ በውል ባልተገለጸ ሁኔታ ገንዘቡ ለኢህአዴግ አራት ድርጅቶች ማለትም ለህወሃት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴን ተከፋፍሏል። ሁሉም ድርጅቶች 80 ሚሊዮን 566 ሺ 221 ብር ደርሶአቸዋል።

ገንዘቡን ለመንግስት ወይም ለከፈሉት ዜጎች መመለስ ሲገባ ድርጀቶች እንዲከፋፈሉት መደረጉ ፣ ኢህአዴግ በተገኘው አጋጣሚና በሰበብ አስባቡ የህዝብ ገንዘብ እየዘረፈ መሆኑን ያመለክታል ሲል ዘጋቢያችን አስተያየቱን አስፍሯል።

No comments:

Post a Comment