Friday, August 14, 2015

በአገራችን በሰሜን ምስራቅ እና በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ መጠኑ እየጨመረ መጥቷል፡፡

ጉዳዩ ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው ተመሳሳይ ድርቅ በመጪው አመት 2008 ዓ.ም በጥቅምት እና በህዳር ወር ሊከሰት እንደሚችል ባለሙያዎች እየጠቆሙ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ገዥው መንግሰት አሁንም የችግሩን አሳሳቢነት ወደ-ጎን በማድረግ ፤የስራዓቱ ደጋፊ እና አቀንቃኝ ከሆኑ ዲያስፖራ ጋር “አስረሽ ሚቺው” እያለ ከበሮ እየደለቀ ይገኛል፡፡
ሆኖም በአገራችን በተለይ በሰሜን ምስራቅ የተከሰተው ድርቅ እንስሳቶችን በከፍተኛ ሁኔታ እየገደለ የሚገኝ ሲሆን ፣በሰው ሕይወት ላይ ቁጥሩ ቀላል የማይባል የሞት አደጋ እያንዣበበ ይገኛል፤በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎች በሰውንት መዳከም እና እስን ተከትሎ በሚመጣ በሽታ እየተጠቁ ናቸው፡፡ ይህ እውነት ከባለፉት ቀናት ዛሬ ላይ ከኢትዮጵያ አልፎ በአለም ላይ መረጃው እየተሰራጨ ይገኛል፤ ይሄን ተከትሎ ገዥው መንግሰት መረጃውን ደብቆ የመያዝ ፍላጎቶ ሊከሽፍበት ችሎአል ፡፡
የመንግሰት ውጥን ሣይሳካ ሲቀር፣ የመንግሰት ኮሚኒኪሽን ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሬዲዋን ሁሴን “ሰባት ሞቶ ሚሊይን ብር በጀት የያዝን በመሆኑ ችግሩን መቆጣጠር እንችላለን” በማላት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ነገሩን ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው እንደሳቸው ገለፃ “ምንም አይነት የዉጪ እርዳታ አያስፈልገንም፣ የዚህን ያህል አሳሳቢ ደረጃ አልደረሰም” ማለታቸው ነው፡፡ እሳቸው ይሄን ይበሉ እንጂ አሁን ላይ የተከሰተው ድርቅ እና በቀጣይ አመት ይከሰታል ተብሎ የተገመተው ድርቅ፣ ከመንግሰት ቅድመ ዝግጅት ማነስ እና የእርዳታ ድርጅቶች መንግሰት በተለመደው መንገድ እየተከላከለ የሚቀጥል ከሆነ፤ አገራችን አስከፊ ሁኔታ ውስጥ የሚከት ነው፡፡ መንግሰት 7መቶ ሚሊየን ብር መደብኩ ይበል እንጂ፣በመንግስት የአሰራር ብልሹነት እና ስር ከሰደደው ሙሱና አንፃር ችጉሩን የቱንም-ያህል ፈቀቅ እንደማያደርገው እውን ነው ፡፡
መንግሰት በተለያየ ወቅት ኢትዮጵያ በምግብ እራሷን ችልለች ይበል እንጂ፣ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ጾም አዳሪ ነው፡፡ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ድርቅ ተከስቶ መንግስት እርዳታ አያስፈልግም ችግሩን መቋቋም እችላለለው በማለቱ፤ አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ ማድረጋ ባለመቻላቸው በሰው እና በእንስሳ ላይ ቁጥሩ ቀላል የማይባል ሞት ተከስቷል፡፡
ድርቁ ሊከሰት የቻለበት ዋና ምክንያት ከአለም አቀፍ የአይር ንብረት ለውጥ ጋር በተገናኘ ነው፡፡ በጠንካራ የመንግሰት አስተዳደር እራሳቸውን ላዋቀሩ በሌሎች አገራት፣ ይህ አይነቱ ድርቅ በሚከሰትበት ወቅት ከመንግሰት የመጠባበቂያ በጀት እና የእህል ክምችት በመጠቀም ችግሩን ለመቋቋም ጥረት ይደረጋል፡፡ እንዲህ አይነቱ መሠረት የሌለው መንግሰት እና ሕዝብ ደግሞ በለጋሽ አገራት የገንዘብ ድጎማና የምግብ እርዳታ ይደረጋል ፡፡ በተለይ ደግሞ አምባገነን መንግስታት በሚመሩት አገር የደርቅ ችግር በሚከሰትበት ወቅት ችግሩን አፍኖ መያዝ ዋንኛ መገለጫቸው ነው፡፡ እንደምክንያትነት የሚነገረው “እረዳት አያስፈልገንም እራሳችን ችለናል” የሚል ባዶ ቀረርቶ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment