Tuesday, August 18, 2015

የሙያ ብቃት ምዘና በአመለካከትና ክህሎት ሰፊ ክፍተት እንዳለበት ተጠቆመ፡፡

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላ ሃገሪቱ በ2001 ዓ.ም የተቋቋመው የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የታሰበለትን ሃገራዊ ፋይዳ በተገቢው ሁኔታ ለማድረስ እንዳልቻለ የአማራ ክልል የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ የሽዋስ ተናገሩ፡፡

ዳይሬክተሩ በክልሉ በልዩ ልዩ ቦታዎች በተካሄደው ውይይት ለተሳታፊዎች እንደገለጹት በአመለካከትና ክህሎት ዙሪያ ሰፊ ክፍተት አለ ብለዋል።
መዛኝ የኤጀንሲውን ሰራተኞች በየጊዜው ለምዘና ለመላክ የተለያዬ ማባበያ በመቀበልና የጥቅም ትስስር በመፍጠር በተደጋጋሚ የተወሰኑትን በመላክ በተደጋጋሚ ተጠቃሚ ማድረግ በፈጻሚው መስሪያ ቤት በኩል የሚታይ ክፍተት እንደሆነ ዳይሬክተሩ ናግረዋል፡፡ በተመዛኞች በኩልም ታይቷል በማለት የሚገልጹት ሃላፊ፣ ሰልጣኞች በብቃታቸውና ሙያቸው ብቁ በመሆን ተገቢውን ማስረጃ ማግኘት ሲገባቸው ገንዘብ በመስጠት፣በዝምድናና ጾታዊ ግንኙነት በመፈጸም ያልተገባ ማስረጃ ለማግኘት የሚደረገው ጥረት በስፋት ይታይ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
በአጠቃላይ ከዚህም ሆነ ከዚያ የሚታዩ የስነ ምግባር ችግሮች እንዳሉ የሚገልጹት ዳይሬክተሩ፣ በስርአቱ ላይ የሚታዩ የስነምግባር ችግሮች በየደረጃውና በየፈጻሚው አካል ላይ ከመታየት አልፎ አገልግሎቱን በሚያገኙ ሰልጣኞች ላይም አሻራውን በመጣል ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኃላፊው ክህሎት የሌላቸው ተመዛኞች መስፈርቱን አሟልተው የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ለማግኘት የሚያደርጉት ህገወጥ አካሄድ በአገልግሎት ሰጪና በአምራች ደርጅቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያመጣ ተናግረዋል፡፡
በተለያዩ የገዢው መንግስት አመራሮች ድጋፍ እና የውስጥ ለውስጥ የባለቤትነት ድርሻ እንዳለበት ከሚታሙት የሙያ ኮሌጆች በየጊዜው የሚመረቁ ተማሪዎች እስከ ሶስት ጊዜ ተመዝነው ማለፍ የሚሳናቸው መሆኑ የትምህር ቤቶችን የማስተማር ብቃት ማነስ ጥርጣሬ ውስጥ የሚያስገባ መሆኑን ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡

No comments:

Post a Comment