Thursday, August 13, 2015

በሆሳዕና የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታሰሩ

ነኅሴ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከገንዘብ ዝውውር ጋር በተያያዘ ትናንት ነሃሴ 6፣ 2007 ዓም በሃድያ ዞን በሆሳእና ከተማ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ሰዎች ክፉኛ ተደብድበው ሆስፒታል የገቡ ሲሆን፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ደግሞ መታሰራቸውን የአይን እማኖች ገልጸዋል።

በርካታ ወጣቶች አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ መደብደባቸውን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ ሆስፒታል የተኙት አመሻሹ ላይ ወደ እስር ቤት በፖሊሶች ተደግፈው መወሰዳቸውን ማየታቸውን ገልጸዋል።
የተቃውሞው መንስኤ ደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች 6 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ በሰዎች ወደ አዲስ አበባ ከላኩ በሁዋላ፣ አዲስ አበባ ያሉ ሰዎች ገንዘቡን በባንክ ወደ ሆሳእና ሲልኩ፣ የመንግስት ባለስልጣናት በማወቃቸውና ገንዘቡን በመውረሳቸው ነው። ባለስልጣናቱ ገንዘቡ ወደ አገር ውስጥ የገባው በባንክ በኩል ባለመሆኑ መንግስት ማግኘት የነበረበትን ጥቅም አላገኘም በሚል ምክንያት ሲያቀርቡ፣ ህዝቡ ደግሞ ልጆቻችን ለፍተውና በሰው ሃገር ተንከራተው የላኩት ገንዘባችን ሊወሰድ አይገባውም በማለት ገንዘቡ መወረሱን ተቃውሞአል። ገንዘቡ ከ100 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ለማከፋፈል የተላከ እንደነበር ታውቋል።
በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለተሻለ ምንዛሬ እንዲሁም ስርአቱን የሚቃወሙ ደግሞ በህጋዊ ባንክ ላለመላክ በሚል ገንዘባቸውን ከባንክ ውጭ ባሉ ዘዴዎች ይልካሉ። ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ድርቅ ያ

No comments:

Post a Comment