Friday, August 14, 2015

አይ አማራ (ሄኖክ የሺጥላ)

ዝም አለሳ ምን ነው
በለሳ ምነው ዝም አለ
ምነው ዝም አለ ጠገዴ 
ማጀቱ አንበጣ አቅፎ ፣ ቀየውን በላው ወንበዴ ።
ምነው ዝም አለ አርማጨሆ
አረ ምን ነካው ጨጨሆ ?
እንደምን ረሳ ሎጋው ና
ሀይሎጋ ሎጋ ሎጋው ወንድ ልጅ
ክንድ የሌው ዘር የሳት እጅ !
አረ ፍጃቸው ፣ ንዳቸው
ቦሀ- ክፍት -ፍንጃል ናቸው
አንተ ተነስ እንጂ ዛሬ
እነሱንስ እንጃላቸው !
ታዲያ ምነው ዝም አለ አገው
የቆላ ዝምብ ፣ ትኩስ ደሙን
በቆመበት ሲጠርገው ?
በለማኝ ፣ በአንበጣ መንጋ
ድፍን ሀገሬው ሲወጋ
በእጣቢ ፣ በውራጅ ገመድ
ታሪክ ባህሉ ሲነገድ
ምነው ዝም አለ አማራው
ነቅንቆ ፣ ጦሩን ቢያዋራው
ባክህ ከጉና ላይ ሁነህ ጥራው
ከሊማልሞ ተራራ


ከላሊበላ መቅደስ ስር
ከጎጃም ፣ ከበላይ ዋሻ
ድጋሚ ቃልህ ይታሰር
ወደ ጫካው ፣ ወደ ዋሻው
በል ገስግሰህ ቶሎ ብረር !
ምነው ዝም አለ ሳይንቱ
የጋፋት ትንታግ እሳቱ
የመቅደላ ምጥ ፣ ኩራቱ
የክብር አክሊል ጥይቱ
ሽጉጡን መዞ ያልወጣው
ጠላቱን ደፍቶ ያልቀጣው
ለምንድን ነው ?
ምነው ዝም አለ ያ ቀዬ
እብሪት በደጁ ሲሰለፍ
ልጁ በፊቱ ሲገረፍ
ካገር ከምድሩ ሲገፋ
ዘሩ በመርፌ ሲጠፋ
ምነው ዝም አለ አማራው
ያን ወንድነቱን ምን ገራው !
በል ጥራው !
ከቋጥኙ ከተራራው
ከአምባው ጫፍ ላይ ከከተማው
ከስርጡ ፣ ከገደሉ ጫፍ
እስኪ እንቁም እንበል ዘራፍ !
ከዋልድባ ቆላድባ
እንዲጥለው እያደባ
ከግሸን እስከ ራስ-አምባ
ተነስ በለው ያንተን እንባ
ተካው በዲሞትፈርህ
ነቅንቀው በ-ቁጡ ደምህ
ዝም አትበል ፣ በል ይወቅህ
ለማኝ እኮ ነው የናቀህ !
ውቃው !
አማራ በደምህ ዛሬም
በማንነትህ ስትሞት
በይሉኝታ ፣ በአብሮነት
ከመቃብር ስትከተት
ዝምታህን የማትገለው
ፍራትህን የማትጥለው
የህብረት ድንኳንህን
አለት ምሰህ የምትተክለው
ለምንድን ነው ?
አማራ ያገር አፈሩ
የታሪክ ቤት ፣ ነብስ አየሩ
የህልውና መሰረት
የኢትዮጵያዊነት አንዱ ቤት
አማራ አርሰህ ባበላህ
ነጭ ጤፉን ፣ ከዘንጋዳ
ማሽላውን ከገብስ ጋ
ወይፈኑን ፣ ሰጋር በቅሎውን
ጊደሩን
ቦራ ሴደሩን
እንደ ከዋክብት በምድሩ
እንደ ሴደርማ አሰልፈህ
ያጎረስክበት እጅህ
የዘረኛ እሳት አቀፈ !
እና ምነው ዝም አልክ
ቁጣህን ዛሬም ይሉኝታ
እምነትህ አስተዳደግህ
ጉርብትናህ ቢይዝህም
ያንተ ፍቅር ላንድ አንተ ግን
አንዲት አልጠቀመህም !
ይኸው የነገሱትም
መንገስ የሚመኙትም
ይሄም ያም ያንተ ጠላት ነው
የገደለኝ አማራ ነው
ይላል !
ስብሰባው ፣ ደባው ዱለታው
ለማደግ ሳይሆን ለመማር
አንተን ለማጥፋት ለመቅበር
እንደሆነ አልገባህም ?
አንተ ግን ዛሬም ስለ ፍቅር
ስለ ጉርብትና እና ዝምድና
አብሮ ስለመኖር አውራ !
አይ አማራ !
ይቀጥላል

No comments:

Post a Comment