Thursday, August 13, 2015

በደቡብ ወሎ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ሰዎች ተገደሉ

ነኅሴ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ፣ ነሃሴ 7 ፣ 2007 እኩለ ቀን ላይ በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ፣ ፖሊሶች በወሰዱት እርምጃ እስካሁን ባለው መረጃ 2 ሰዎች ሲገደሉ፣ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎች ቆስለዋል። ረብሻው እስከ አመሻሽ ቀጥሎ ከደሴ የተነሱ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ አካባቢው ደርሰው ጥበቃ እያደረጉ ነው። በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ሁለት ፖሊሶች ክፉኛ ቆስለው በአሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ናቸው።

ነዋሪዎች እንዳሉት የተቃውሞው መንስኤ በወረዳው ሊገነባ የነበረው የመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ ወደ ሌላ ቦታ መዛወሩን ተከትሎ ነው። የብአዴን ሊ/መንበርና ም/ል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከምርጫ በፊት ወደ አካባቢው በመሄድ የዩኒቨርስቲውን የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጡ ሲሆን፣ ምርጫው ከተጠናቀቀ በሁዋላ ዩኒቨርስቲው እንደማይሰራና ለመካነሰ ሰላም ወረዳ መሰጠቱ ተነግሯል።
ነዋሪዎች እንደሚሉት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተዘግተዋል። የወረዳው ባለስልጣናት በፖሊሶች እየተጠበቁ ነው። የፖሊስ መኪኖች ተሰባብረዋል፣ ወደ ተለያዩ አካባቢ የሚሄዱ መኪኖችም ቆመዋል።

No comments:

Post a Comment