Monday, August 10, 2015

ትላንት ምሽት በአዲስ አበባ የ3 ወጣቶች አስክሬን ኩሬ ውስጥ ተገኘ…

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ላንድሮቨር ማዞሪያ፣ መሳይ ካባ በተባለ ቦታ ነው ወጣቶቹ ህይወታቸው አልፎ የተገኙት ተብሏል፡፡
በአካባቢው ለመንገድ ስራ ድንጋይ ለማውጣት የተቆፈረ ከ7 እስከ 9 ሜትር ርዝመት ያለው ጥልቅት መለስተኛ ሐይቅ ፈጥሯል፡፡
ሁለቱ 20 አንዱ ደግሞ 25 አመታቸው ነው የተባሉ 3 ወጣቶች የገቡበት ምክንያት ባይታወቅም የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን ከአካባቢው ነዋሪ በደረሰው ጥቆማ ትላንት ምሽት 3 ሰዓት ላይ የወጣቶቹን አስክሬን አውጥቷል፡፡
ከወጣቶቹ አንዱ ልብሱን አወላልቆ የነበረ ሲሆን ሁለቱ ግን ልብሳቸውን እንዳደረጉ፣ ጫማቸውንም እንደተጫሙ መገኘታቸውን የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አዳነ አብርሃ ነግረውናል፡፡
ወጣቶቹ አስክሬናቸው ምሸት 3 ሰዓት እንዲወጣ ቢደረግም በጊዜ ሳይገቡ እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡
የአሟሟታቸው ምክንያትም በፖሊስ እየተጣራ ነው ተብሏል፡፡

No comments:

Post a Comment