Wednesday, August 5, 2015

የኦጋዴን ነጻ አዉጪ ጦር ጉዳት አደረስኩ እያለ ይገኛል

ሰበር የጦርነት ዜና።
የኦጋዴን ነጻ አዉጪ ጦር ጉዳት አደረስኩ እያለ ይገኛል
Ogaden National Liberation Front (ONLF) ከኦጋዴን ነጻነት ግንባር መካከለኛ አዛዥ መምሪያ ክፍል የወጣዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ ሸበሌ ተብሎ በሚጥራዉ ክልል በተለያዩ ጊዜያትና ወቅቶች ጦር የገጠመ ሲሆን በተለይም በ 30/7/15 ቦሆልካቢዮካዴ በተባለዉ ስፍራ 15 የወያኔ ወታደሮችን መግደሉንና 25 ማቁሰሉን ሲያስታዉቅ በተጨማሪ በ 27/7/15 በመስራቃማዉ ባንያሬ 8 ሲገደል 6 ደግሞ ማቁሰሉን አያይዞ ጠቅሷል ይህ የኦጋዴን ነጻ አዉጭ የተባለ የነጻነት ግንባር ወደ አርበኞች ግንቦት 7 እንዲቀላቀል በሚደረጉ ግንኙነቶች ዙሪያ ወደ ስምምነት ይመጣሉ ተብሎ ከሚገመት አንዱ ነዉ።
ተለያይቶ በሚደረግና ሐገርን ሊበታትን በሚችል መልኩ ወያኔ የሰራብንን የመለያየት መንፈስ ለማስወገድ በአንድነት መስራት አልብን የሚለዉን የአርበኞች ግንቦት 7 መርህ ብዙ የፖለቲካ ድርጅቶች እየተቀበሉትና እየተከተሉት ባለበት በዚህ ወቅት በተለያየ መስመር እየተሰነዘረ ያለዉን ጥቃት ወያኔ መከላከል ተስኖታል። በመሆኑም በሰሞኑ የወያኔ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች የጦርነት ቅስቀሳ መዝሙራቸዉን ጀምረዋል።

No comments:

Post a Comment