Wednesday, August 5, 2015

በሳዑዲ አረቢያ ሁለት ኢትዮጵያውያን አንገታቸውን ተቀሉ

ሐምሌ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገሪቱ ደቡባዊ ምዕራብ ጀዛን ከተማ ውስጥ በአንድ ሳውድ አረቢያዊ ዜጋ ላይ ዝርፊያና ግድያ ፈፅመዋል ተብለው የተከሰሱት ሁለቱ ኢትዮጵያዊያን ፣ አረጋዊ አልዶ ኃ/ማሪያም እና ሃዲሽ ዘላለም ናቸው። ሁለቱ ኢትዮጵያውያን አንገታቸውን ተቀልተው የሞት ፍርድ ተፈፅሞባቸዋል ሲል የሳዑዲ አረቢያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስቴሩን ጠቅሶ ታይምስ ላይቭ ዘግቧል።

በሌላ ወንጀል የተከሰሰው የአገሪቱ ዜጋ የሆነው ሙሻሻ ሃርሲም በጥይት ሰው በመግደሉ አንገቱ እንደተቀላ ሚንስቴሩ አክለው ገልፀዋል።በሳዑዲ አረቢያ በያዝነው ዓመት ብቻ 113 ሰዎች በሞት እንደተቀጡና በአገሪቱ ዜጎችና በውጭ ስደተኞች ላይ የሚፈፀመው የሞት ቅጣት ብያኔ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 130 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል በሪፖርቱ ገልፅዋል።

No comments:

Post a Comment