Friday, August 14, 2015

የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ቁጣ ተጠናክሮ ቀጥሏል::

ከዳንሻ አከባቢ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት በቅርቡ በሕወሓት ተላላኪዎች እና በወልቃይት ጠገዴ ነዋሪዎች መካከል የተደረገው የሽምግልና ሂደት ተከትሎ አለመስማማቶች እየሰፉ በመምጣታቸው የዳንሻ ነዋሪዎች በከፍተኛ ቁጣ ለተቃውሞ ሰልፍ መዘጋጀታቸው ታውቋል::በወልቃይት ጠገዴ ሰሞኑን የሕዝቡን ቁጣ ማየሉን ተከትሎ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከጎንደር በመነሳት ሁመራ ዳንሻ አብርሃጅራ አከባቢ ከፍተኛ ዝመናዊ መሳሪያዎች በአይሮፕላን መተው እየተራገፉ ሲሆን እንዲሁም ብዛት ያላቸው ወታደሮች ባከባቢው እየሰፈሩ መሆኑ ታይቷል::

ነሃሴ 3 2007 ከአማራ ክልል እና ከትግራይ ክልል ሽማግሌ ተብለው የ
ተመረጡ የመንግስት ባለስልጣናት ባልተሳተፉበት የሽምግልና ስብሰባ ላይ በተነሱ ነጥቦች ስምምነት አለመደረሱ የታወቀ ሲሆን በስብሰባው የወልቃይት ሕዝብ እኛ አማሮች እንጂ ትግራዮች አይደለንም ልጆቻችን በአማርኛ መማር አለባቸው የሚል ጥያቄ ያነሱ ቢሆንም ከትግራይ የመጡ ሽማግሌዎች የኛ ልጆች ናቹ አማሮች አይደላችሁም ስላሉ በመካከላቸው ከባድ አለመግባባቶች ተከስተው እንደነበር ስብሰባውን የተካፈሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል::አለመግባባቶች ሲከሰቱ በስብሰባው የተገኘው 300 ሰው በመናቅ የትግራይ ተሰብሳቢዎች ሽምግልናውን አፍርሰው መለየታቸው ሲታወቅ ከሁለቱም ወገን ለሽምግልናው ውይይት የተመደቡ 30 ሰዎች ስምምነት ላይ መድረስ እንዳልቻሉ ተጠቁሟል::
ልጆቻችን በአማርኛ መማር አለባቸው የሚሉት የወልቃይት ጠገዴ ሕዝቦች በሽምግልናው በኩል በቂ መልስ ባለመገኘቱ ለጥገዴ አስተዳዳሪ ጥያቄው መቅረቡ ታውቋል::ትምህርቱ በአማርኛ የማይሰጥ ከሆነ ልጆቻችንን ወደ እናንተ ትምህርት ቤት አንልክም ሲል ሕዝቡ ቁርጡን ተናግሯል::በወልቃይት ጠገዴ አከባቢ ስርአተ ትምሕርቱ አማርኛ ይሁን የሚለው ጥያቄ ለመመለስ በሕወሓት የተመደበው አስተዳዳሪ ቢከብደውም ከአቅሙ በላይ ስለሆነ ለአማራ እና ትግራይ ክልል ባለስልጣኖች ጥያቄው ሳይላክ እንደማይቀር ተገምቷል::ከክልሎቹ እስከ ነሃሴ 12 ድረስ መልስ እንደሚጠበቅ እና የሕዝቡ ቁጣ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ወያኔን እንደጣለው በአከባቢው የሚደረጉ ወታደራዊ እንቅስቃሰዎች ውጥረቱ እንዲያይል አድርገውታል::#ምንሊክሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment