Monday, August 31, 2015

የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙት

1eac1-pg7-logo

የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት
‪#‎ስምንት‬ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በኢትዮጵያና ሱዳን አዋሳኝ ድንበር መሬት ላይ ኩላሊታቸውን ለመዝረፍ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተገለፀ፡፡
‪#‎የህወሓት‬ አገዛዝ ሙሉ እምነት ያላሳደረባቸውን የራሱን ሹሞች በደህንነቶቹ እያሳፈነ ወዳልታወቀ ቦታ እያጋዛቸው ነው፡፡
‪#‎ሱዳን‬ ከኢትዮጵያ ግዛት ተጫሪ መሬቶችን ለመውሰድ ለህወሓት አገዛዝ ጥያቄ ማቅረቧን ሄራልድ ትርቢውን የተባለ የሱዳን ጋዜጣ ዘገበ፡፡

ስምንት ኢትዮጵያዊን ወጣቶች በኢትዮጵያና ሱዳን አዋሳኝ ድንበር መሬት ላይ ኩላሊታቸውን ለመዝረፍ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተገለፀ፡፡
ስምንቱ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ወደ አገራችንና ሱዳን ድንበር መሬት የተንቀሳቀሱት የሰሊጥ አረም የጉልበት ስራ በመስራት የዕለት ጉርሳቸውን ለማሟላት ሲሆን እጅግ በጣም ዘግናኝ በሆነ አገዳደል ሁኔታ ለእንጀራ ሲሉ በግፍ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
ስምንቱ ኢትዮጵያዊያን ከተገደሉ በኋላ ሆድ ሆዳቸው ተቀዶ ኩላሊታቸው ሙልጭ ብሎ መዘረፉን አስከሬኖቹን የተመለከቱ የዓይን እማኞች ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡
ስምንቱን የጉልበት ሰራተኛ ኢትዮጵያዊያን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል ኩላሊታቸውን አውጥተው የወሰዱት የሱዳን ዜጎች መሆናቸውን ምንጮቻችን ጨምረው አስታውቀዋል፡፡
የህወሓት አገዛዝ ሙሉ እምነት ያላሳደረባቸውን የራሱን ሹሞች በደህንነቶቹ እያሳፈነ ወዳልታወቀ ቦታ እያጋዛቸው ነው፡፡
ከትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ውጭ የሆኑ የህወሓት የሲቪልና የፀጥታ ሹሞች በድንገት እየተሰወሩ የሚገኙ ሲሆን አፈናው በመከላከያና በፖሊስ ኃይሎች ውስጥ በተለየና በተጠናከረ እንዲሁም ምስጢራዊነቱን በጠበቀ ሁኔታ መቀጠሉ እየተነገረ ነው፡፡
በመከላከያ ውስጥ በተለያዩ ዕዞች ከትግራይ ብሄር ተወላጆች ውጭ የሆኑ ወታደራዊ አዛዦች በመብራት እየተፈለጉ በመለቀም ታፍነው ወዳልታወቀ ቦታ እየተወሰዱ ነው፡፡
ለአገዛዙ ታማኝ እንዳልሆኑ የሚጠረጠሩ ከፍተኛ እና ዝቅተኛ የፖሊስ ሹሞችም እንዲሁ አፈናው በተመሳሳይ ሁኔታ በርትቶባቸዋል፡፡ ከሰሞኑ የጭልጋ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ በህወሓት ደህንነቶች ታፍኖ መወሰዱ እና አሁን የት እንደሚገኝ አድራሻው ፈፅሞ እንደማይታወቅ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ተናግረዋል፡፡
የህወሓት ዘረኛ ቡድን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እያደረሰው ከሚገኘው ከዚህ ሰዎችን አፍኖ መሰወር ዜና ጋር በተያያዘ አቶ ሙሉቀን ገብሩ የተባለ ወጣትና በባጃጅ ሹፍርና ስራ የሚተዳደር የሸዲ ነዋሪ በቅርቡ በደህንነቶች ታፍኖ ተወስዶ የደረሰበት አልታወቀም፡፡
ሱዳን ከኢትዮጵያ ግዛት ተጫሪ መሬቶችን ለመውሰድ ለህወሓት አገዛዝ ጥያቄ ማቅረቧን ሄራልድ ትርቢውን የተባለ የሱዳን ጋዜጣ ዘገበ፡፡
ሱዳን ያነሳችው የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ከስድስት መቶ ሺህ ሄክታር በላይ “የአማራ ክልልን” መሬት ወደ ገዳሪፍና ቡሉ ናይል ግዛቶች አስገብቶ ለማጠቃለል በማለም ነው፡፡
ጥያቄው የቀረበለት ራሱን እንደመንግስት የሚቆጥረው የህወሓት አገዛዝ ጠብመንጃ ካነሱ የነፃነት ኃይሎች እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ለህልውናው ስለሚያሰጋው ከሱዳን መንግስት ጋር ግጭት ውስጥ ላለመግባት የሱዳንን መንግስት ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ለማርካት ውስጥ ለውስጥ በምስጢር እየሰራ መሆኑ ከውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
የህወሓት አገዛዝ ከዚህ ቀደም እጅግ በጣም ሰፋፊና ለምየሆኑ “የአማራ ክልል” መሬቶችን ከምስኪን ገበሬዎች ነጥቆ ለሱዳን መንግስት እጅ መንሻ መስጠቱ አይዘነጋም፡፡

No comments:

Post a Comment